ሻምበል መማር ጌትነት በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ልዩ ስሙ ወርቅ ዋሻ በተባለ አካባቢ በግፍ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ አስከሬኑ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

ሻምበል መማር ጌትነት በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ልዩ ስሙ ወርቅ ዋሻ በተባለ አካባቢ በግፍ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ አስከሬኑ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት21 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰኔ 15/2011ዱ የባለስልጣናት ግድያ እድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ሻምበል መማር ጌትነት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ አስከሬኑ ተገኝቷል። ጥቅምት 18/2015 ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በአሰቃቂ መልኩ በጥይት እና በስለት ጭምር ግድያ የተፈጸመበት ሻምበል መማር ጌትነት አስከሬኑ በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ወርቅ ዋሻ በተባለ አካባቢ አስፓልት ላይ ተጥሎ መገኘቱን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል። መቄት ወረዳ በወቅቱ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ባለማግኘቱ በትክክል ያልታወቀ ይበለው እንጅ አስከሬኑ የሻምበል መማር ጌትነት መሆኑ ታውቋል። አሁን ላይ አስከሬኑም ከወርቅ ዋሻ ወደ ወደ ሸድሆ መቄት ሆስፒታል ተወስዶ የሚረከብ ቤተሰብ እየተጠበቀ መሆኑን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ካነጋገረው የመቄት ፖሊስ ለማወቅ ችሏል። በሰኔ 15/2011ዱ የባለስልጣናት ግድያ ከተከሰሱት እና በሌሉበት በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እድሜ ልክ ከተፈረደባቸው መካከል አንዱ የሆነው ሻምበል መማር ጌትነት በግፍ ተገድሎ አስከሬኑ ወድቆ የተገኘው በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ወርቅ ዋሻ፣ ከደቡብ ጎንደር ዞን ጨጨሆ መድሃኒያለም አዋሳኝ አካባቢ መሆኑ በፖሊስ ተመላክቷል። “ሻምበል መማር ጌትነት በታህሳስ 13/2012 በድሬድዋ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል” በሚል በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ተዘግቦ እንደነበር በማስታዎስ ግድያው ከእስር ቤት በማስወጣት ተፈጽሞ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ሲያጋሩ ለማስተዋል ተችሏል። በመቄት ወረዳ የፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጌታቸው አለሜ እንደገለጹት በወረዳው ደብረዘቢጥ ቀበሌ፣ በላይ ጋይንት ወረዳና መቄት ወረዳ አዋሳኝ ልዩ ስሙ ወርቅ ዋሻ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ መንስኤውና ገዳዩ ባልታወቀ ሁኔታ ጥቅምት 18/2015 ዓ.ም በህዝብ ጥቆማ ከአስፓልት መንገድ ዳር ከውሃ ተፍሰስ ቱቦ ላይ ከረፋዱ አራት ስዓት ላይ አስከሬኑ ወድቆ መገኘቱን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አጋርተዋል። ወረዳው ለበለጠ መረጃም በስልክ ቁጥር ፦ 09 14 06 48 32፣ 09 87 77 84 59 እና 0921 52 39 37 በመደወል መረጃ ለማግኘት እንደሚቻል አስታውቋል። በተያያዘ ነዋሪነቱ በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ መና መቀጥዋ የሆነው የሻለቃ አስቻለው ደሴ ጀግና የትግል አጋር እንደነበር የተነገረለት ፋኖ ቅዱስ ደሴ ጥቅምት 12/2015 መንገድ ላይ ጠብቀው በመቆዬት ተኩስ በከፈቱበት የጉና በጌምድር ፖሊሶች አምጃዬ በተባለ ቦታ መገደሉን እና በተኩስ ልውውጡም ከፖሊሶች የተገደለ እና የቆሰሉ ስለመኖራቸው አሚማ ከአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጧል። ፋኖ ቅዱስ ባለፈው ዓመት በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ከተማ ላይ በተፈጠረ እለታዊ የግል ግጭት ምክንያት ባበይ በተባለ ፋኖ ላይ ግድያ መፈጸሙን እና እርቅ ሰላም ሳይፈጸም መቆየቱን ምንጮች ተናግረዋል። በተያያዘ በፋኖ ቅዱስ ደሴ መገደል በእጅጉ ያዘኑ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ወዳጆቹ ጥቅምት 20/2015 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በሻማ ማብራት ስነ ስርዓት በማስታወስ ነፍስ ይማር ብለዋል። ከወራት በፊት በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ከደቡብ ወሎ ፋኖ መሀመድ የተባለ አባሉ ሀርቡ ላይ ከታሰረ በኋላ በፖሊስ በተፈጸመበት ከፍተኛ ድብደባ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል። በተመሳሳይ በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ እንዲሁ ደሳለኝ አያል የተባለ ወጣት ጥቅምት 8/2015 በእስር ላይ እያለ በፖሊስ በተፈጸመበት ድብደባ ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply