ሼህ የሱፍ በኦነግ ተገደሉ  የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪ ቄሮዎች በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚኖሩ አማራዎች ላይ የሚፈፅሙት ግድያና ማፈናቀል ዛሬም እንደቀጠለ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናገ…

ሼህ የሱፍ በኦነግ ተገደሉ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪ ቄሮዎች በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚኖሩ አማራዎች ላይ የሚፈፅሙት ግድያና ማፈናቀል ዛሬም እንደቀጠለ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናገ…

ሼህ የሱፍ በኦነግ ተገደሉ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪ ቄሮዎች በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚኖሩ አማራዎች ላይ የሚፈፅሙት ግድያና ማፈናቀል ዛሬም እንደቀጠለ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉድሮ ዞን በአሙሩ ወረዳ ዋሊ ልጉማ በተባለ ቀበሌ የሚንቀሳቀሱ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪ ቄሮዎች ሼህ ዩሱፍ የተባሉ አማራን ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 7 ሰዓት አካባቢ በጥይት ገድለዋል። ይህን ተከትሎም በዋሊ ልጉማ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ ከ30 በላይ አማራዎች ተፈናቅለው መውጣታቸው ተገልጧል። ትጥቅና ስንቅ የሚያቀርቡ በተለይ ደግሞ ወደ ጫካ በማቅናት በሬ እያረዱ ለኦነግ ሸኔዎች ከሚቀልቡት የዋሊ ልጉማ ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል መርጋ ታፈረ፣ደረጀ አስፋው፣ጀልዲ ነገሮ እና አቶ ዋሴ እንደሚገኙበት መረጃ ቢሰጣቸውም የአካባቢው የፀጥታ አካላት እያወቀ በህግ ለመጠየቅ አልፈለጉም፤ እንዲያውም እነእገሌ ናቸው የጠቆሙ በሚል ማሳደድ የተለመደ ሆኗል ብለዋል። በዱበሪ እና በጃርሶ በርሀ እንደፈለጉ ይንቀሳቀሳሉ፤ ሼራ ወጥረውም እየኖሩ መሆናቸውም ተጠቁሟል። በተመሳሳይ ኦነግ ሸኔዎች ትናንት ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ አቶ መሀመድ ሀሰን የተባሉ አማራን በኪረሞ ወረዳ ባጅን ማርያም በተባለ ቀበሌ ገድለዋል። በዚህ ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰ ሰብላቸውን ሳይሰበስቡ ለመፈናቀልና በዱር ለማደር እየተገደዱ መሆኑን ገልፀዋል። በአካባቢው ያሉ የፀጥታ አካላት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ አይደሉም፤ መከላከያ በመነሳቱ ተቸግረናል ብለዋል። የአቶ መሀመድ ሀሰንን አስከሬን አንስቶ ምርመራ የሚያደርግ የመንግስት አካል ባለመገኘቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ስርዓተ ቀብራቸውን ስለመፈፅማቸው ተገልጧል። ከዚህም በተጨማሪ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓም ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ የጦር መሳሪያቸውን ለመግፈፍ ሲሉ ኦላኒ ነመራ እና ቅላጤ ዋጅራ የተባሉ የጊዳ ወረዳ ነዋሪዎችን በጥይት ገድለዋል፤ መሳሪያቸውንም ወስደዋል ነው የተባለው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply