ሽሬ ከተማ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳለ በቦታው የሚገኙ የሰላም ሚኒስቴር የሰላምና ሰብዓዊ ድጋፍ ቡድን አባላት ገለጹ

ሽሬ ከተማ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳለ በቦታው የሚገኙ የሰላም ሚኒስቴር የሰላምና ሰብዓዊ ድጋፍ ቡድን አባላት ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሽሬ ከተማ በአሁኑ ሰዓት ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳለ በቦታው የሚገኙ የሰላም ሚኒስቴር የሰላምና ሰብዓዊ ድጋፍ ቡድን አባላት  ገልጸዋል።

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋም የአደጋና ስጋት መከላከል ኮሚሽን ባልደረቦች ጋር በምዕራብ ግንባር በአካል በመገኘት ሰብዓዊ ድጋፍ በማስተባበር ላይ ይገኛሉ።

ጄነራል ብርሀኑ ጥላሁን በሰሜን ዕዝ የምዕራብ ግንባር የሎጀስቲክስ ኃላፊ እንዳሉት የሽሬ ከተማ እንቅስቃሴ ሰላማዊና እና ማህበረሰቡ ያለስጋት እየተንቀሳቀሰ እና የዕለት ተዕለት ተግባሩን እያከናወነ እንዳለም ተናግረዋል፡፡

አክለውም በህግ ማስከበሩ ሂደት ለተፈናቀሉና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖቻችችን እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ጄነራል ብርሀኑ ጦርነት አይበጅም ብለው ጠላትን በማሳፈር ከመከላከያ ሠራዊት ጎን ለቆመው የትግራይ ህዝብና እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተገኘው ድል እንኳን ደስ አላችሁ፤ ሀገርን በታላቅነቷ ለማስቀጠል ህግን የማስከበርና የሀገር ህልውና ዘመቻ ላይ ለተደረገው እና እንዲሁም እየተደረገ ላለው ከፍተኛ ርብርብና ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

በሂደቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገ የዕለት ደራሽ ሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ሽሬ ከተማ እየገባ ይገኛል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ሽሬ ከተማ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳለ በቦታው የሚገኙ የሰላም ሚኒስቴር የሰላምና ሰብዓዊ ድጋፍ ቡድን አባላት ገለጹ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply