ሽሮሜዳ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሽሮሜዳ አምባ ትምህርት ቤት አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን የማቾች ቁጥር ስድስ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/YYkOD2gnyRptvH5ojkzvFYmVRlF8J7Nc-3Qw3NWGE2QTf03w6I_OyQ7K1QushV0jzimbRxFjIUdWZKzXxpVyMklOI_mATVT0y8VEPMIOWf7UMVVKoaKy812eR6QZdY094gII9BrYDUqBL3UXeeGeklqE6ecW4rBU9CUo_YX98hye317KQD8vmb9gSSiKixFDXDsNQx_qCR5xJkDhcOx5VR86zKo4png6Vyr-lb9kA2O2zqvWYfhk5_b1H2caDw6Rk4-OODvu829OF8FiumHZC6Z9-iTvUwAbyOJwyPtsLy94U0RFG-SBYIVluL4c4YjYDSAJqhKcsafM-VbLLxfadg.jpg

ሽሮሜዳ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሽሮሜዳ አምባ ትምህርት ቤት አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን የማቾች ቁጥር ስድስት መድረሱ ተነግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት፣ የማቾች ቁጥር ከዘህም ከፍ ሊል የሚችልበት አጋጣሚ አለ ብለዋል፡፡

አደጋው የደረሰው የታክሲ አገልግሎት በሚሰጥ በተለምዶ ሚኒባስ ተብሎ የሚጠራው ተሸከርካሪ ላይ ነው ብለውናል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በቦታው ተገኝተው የነፍስ አድን ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ሲሉ ኢንስፔክተር ማርቆስ ለጣበያችን ተናግረዋል፡፡
የአደጋውን መረጃ እንደተጠናቀቀ ሙሉ መረጃውን የምናቀርብ ይሆናል፡፡በተከሰተው አደጋ ሁለት ተማሪዎችን ጨምሮ በ6 ሰዎች ላይ የሞት አደጋ እንዲሁም ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ እና ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡

በአደጋው የደረሰው የጉዳት መጠንና መንስኤውን ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ፖሊስ አሳውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply