“ቀናችን ያበሩልናል ብለን የጠበቅናቸው መንግስት ተብዬዎችም ቀናችን እስኪ ጨልም እየጠበቁን እና ቀናችን እንዲመሽ እያዘናጉን እንደሆነም አውቀን እርማችን አውጥተናል።” ሲል የአማራ ወጣቶች ማ…

“ቀናችን ያበሩልናል ብለን የጠበቅናቸው መንግስት ተብዬዎችም ቀናችን እስኪ ጨልም እየጠበቁን እና ቀናችን እንዲመሽ እያዘናጉን እንደሆነም አውቀን እርማችን አውጥተናል።” ሲል የአማራ ወጣቶች ማ…

“ቀናችን ያበሩልናል ብለን የጠበቅናቸው መንግስት ተብዬዎችም ቀናችን እስኪ ጨልም እየጠበቁን እና ቀናችን እንዲመሽ እያዘናጉን እንደሆነም አውቀን እርማችን አውጥተናል።” ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ እንደሚታወቀው የአብይ አህመድ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ የአማራው ግፍ እና መከራ መልኩን እና ይዘቱን ቀይሮ ተባብሶ ስለመቀጠሉ የገለፀው የአማራ ወጣቶች ማህበር የደረሰብንን መገፋት እና በዘር የተጨፈጨፍንበትን የደም አውድማ እንዘርዝር ብንል የሚችልልን ገፅ የሚፅፍልን ብዕር አይኖርም ሲል የችግሩን ግዝፈት አመልክቷል። ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በመሆን አገሩን በደሙ እና ባጥንቱ ያቆመው አማራ፣አማራ መሆን ሀፂያት እና ወንጀል ሆኖበት በእዬ ስርቻው ሲገረፍ፣በእዬ አደባባዩ እንደ ሽንኩርት ሲከተፍ፣ሀብት ንብረቱን በጠራራ ፀሀይ ሲዘረፍ፣የሰውነት ክብሩን ሲነጠቅ-ማየቱ የአደባባይ ሀቅ እና እየተለመደ የመጣ የዘወትር ተግባር ሆኗል ነው ያለው የአማራ ወጣቶች ማህበር በመግለጫው። “ከነገ ዛሬ በአማራ ላይ ያጋደለችው ጀምበር ትቃናለች ብለን ደረት እየደቃን እና ፊታችን እየፈጀን ብንጠብቅም ጀምበሯ ግን ይባስ ብላ ወደ መጥለቂያዋ አድማስ ተቃርባለች።” ያለው ማህበሩ “ቀናችን ያበሩልናል ብለን የጠበቅናቸው መንግስት ተብዬዎችም ቀናችን እስኪ ጨልም እየጠበቁን እና ቀናችን እንዲመሽ እያዘናጉን እንደሆነም አውቀን እርማችን አውጥተናል።” ሲል አክሏል። አማራ ወቅቱን በዋጀ እና የጠላትን ጥርስ በአማከለ መልኩ ከተጋረጠበት ችግር ለመውጣት እንዲመክር እና ጠላትን ለመመከት ዝግጅት እንዲያደርግ ሲል ነው የአማራ ወጣቶች ማህበር ጥሪ ያቀረበው። የመንግስትን ህገወጥነት እና ሸፍጥ ለአለሙ ማህበረሰብ ለማድረስ መዘጋጀቱን ያስታወቀው ማህበሩ መርጦ የሚያስገድለን እንጂ መርጠነው የሚያስተዳድረን መንግስት አለመኖሩ ግን ሊሰመርበት እና ሊወሳ ይገባል ብሏል። ቀጣይ የሚኖሩንን የትግል ስልቶች እንደ አስፈላጊነቱ በተገቢው መንገድ የሚያሳውቅ መሆኑን የጠቆመው የአማራ ወጣቶች ማህበር የሀገር ጉዳይ የሚያሳስበው እና የአማራው ጅምላ መጨፍጨፍ የቆረቆረው ማንኛውም አካል ከጎናችን እንዲሆን እና የተቻለውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ ጥሪያችን እናስተላልፋለን ብሏል። “ከባህላችን ውጭ የሆነ ሞትን ቆሞ ከመቀበል፣ቆሞ መሞት የፊትም የኋላም ታሪካችን ድል ነው።” ሲል ዋና ጽ/ቤቱን አዲስ አበባ ያደረገው የአማራ ወጣቶች ማህበር አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply