ቀን 05/02/2014 ዓ.ም ለኢትዮጵያ መገናኛን ብዙኃ ባለስልጣን ጉዳዩ፡- በስራ ላይ ስለተፈጠረ ስህተት ይቅርታን ይመለከታል፡- በቀን 30/01/2014 ዓ.ም በደቡብ…

ቀን 05/02/2014 ዓ.ም ለኢትዮጵያ መገናኛን ብዙኃ ባለስልጣን ጉዳዩ፡- በስራ ላይ ስለተፈጠረ ስህተት ይቅርታን ይመለከታል፡- በቀን 30/01/2014 ዓ.ም በደቡብ አቸፈር ወረዳ ላሊበላ ከተማ የፋኖ ምርቃት ላይ ስለተላለፈዉ ማህበረሰብን የማይወክል ንግግር በአርትኦት ስህተት የግለሰቡን ሀሳብ ለህዝብ ጠቃሚነቱ እና ጎጅነቱ ሳይመዘን ተዘግቧል ፡፡ ሀሳቡ የጥላቻ ንግግር ይዘት ያለው መሆኑ ብቻ ሳይሆን አሻራ ሚዲያ ከተቋቋመበት ዓላማም ጋር የሚፃረር ሆኖ ስላገኘነው በተሳተፉት ባለሙያወች ላይ ልዩ ልዩ ዲሲፕሊን እርምጃ ወስደናል። ከሠው ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋምና ለተፈጠረው ስህተት መላው የኢትዮጵያ ህዝብና አድማጭ ተመልካቾቻችን ይቅርታ እንጠይቃለን። ግለሠቡ የተናገረውን ሀሳብም ከዩትዩብ ቻናላችን ማንሳታችን እናሳዉቃለን፡፡ አሻራ ሚዲያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply