ቀይ መስቀል ለትግራይ አርሶ አደሮች ማዳበሪያዎችን እያከፋፈለ ነው

https://gdb.voanews.com/801e0000-c0a8-0242-20ed-08da79547e11_w800_h450.jpg

በኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር ትግራይ ውስጥ በግጭት የተጎዱ አርሶ አደሮችን ምርታማነት ለማሳደግ ኤንፒኤስ እና ዩሪያ የተባሉ የማዳበሪያ ዓይነቶችን ለ20ሺ አባወራዎች ወይም 120ሺ ለሚደርሱ ግለሰቦች ማዳረሱን ዛሬ ማኅበሩ ባወጣው የትዊት መልዕክት አስታውቋል፡፡

ማዳበሪያዎቹን የተከፋፈሉት ማኅበሩ ባላፈው ሰኔ በምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡባዊ የትግራይ ዞኖች ያሰራጨውን የምርጥ ዘር ተከትሎ መሆኑንም ቀይ መስቀል አመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply