You are currently viewing ቀደምቶች በታላቅ ተጋድሎ ያቆዯት ኢትዮጵያ ከገጠማት እጅግ ፈታኝ የሆነ የህልውና አደጋ የመታደግ ታላቅ ታሪካዊ ሃላፊነት እና አደራ እንዳለብን የገለጸው ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን…

ቀደምቶች በታላቅ ተጋድሎ ያቆዯት ኢትዮጵያ ከገጠማት እጅግ ፈታኝ የሆነ የህልውና አደጋ የመታደግ ታላቅ ታሪካዊ ሃላፊነት እና አደራ እንዳለብን የገለጸው ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን…

ቀደምቶች በታላቅ ተጋድሎ ያቆዯት ኢትዮጵያ ከገጠማት እጅግ ፈታኝ የሆነ የህልውና አደጋ የመታደግ ታላቅ ታሪካዊ ሃላፊነት እና አደራ እንዳለብን የገለጸው ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን የእንኳን ለአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ 127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ብሔራዊ ኩራት ነው። የዘንድሮውን የ127ኛው የአድዋ ድል በአልን ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደ ሀገር የመቀጠል እጣዋ ከፍተኛ አደጋ ላይ የወደቀበት ወቅት መሆኑን አፅንኦት በመስጠት እና ቀደምት አባቶቻችን በታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት ያቆዩልንን የጋራ ሀገራችንን ከመቼውም ጊዜ በላቀ የመጠበቅ እንዲሁም ከገጠማት እጅግ ፈታኝ የህልውና አደጋ የመታደግ ታላቅ ታሪካዊ ሃላፊነት እና አደራ በኛ ትውልድ ትከሻ ላይ መውደቁን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊሆን ይገባል። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

Source: Link to the Post

Leave a Reply