You are currently viewing ቀደም ሲል ከተከፈተባቸው የሁከት እና ብጥብጥ መዝገብ በዋስ እንዲለቀቁ ሲወሰን እንደገና በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል የተባሉት እነ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው እና ዳዊት በጋሻው ለግንቦት 18…

ቀደም ሲል ከተከፈተባቸው የሁከት እና ብጥብጥ መዝገብ በዋስ እንዲለቀቁ ሲወሰን እንደገና በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል የተባሉት እነ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው እና ዳዊት በጋሻው ለግንቦት 18…

ቀደም ሲል ከተከፈተባቸው የሁከት እና ብጥብጥ መዝገብ በዋስ እንዲለቀቁ ሲወሰን እንደገና በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል የተባሉት እነ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው እና ዳዊት በጋሻው ለግንቦት 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 4/2015 ዓ/ም… አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከተከፈተባቸው የሁከት እና ብጥብጥ መዝገብ በዋስ እንዲለቀቁ ሲወሰን እንደገና በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል የተባሉት እነ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው እና ዳዊት በጋሻው ግንቦት 4/2015 ጠዋት በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ነበር። ተጠርጣሪ የተባሉት ጋዜጠኞችም በሚዲያ አላግባብ ስማችን ጠፍቷል፤ ፖሊስ ስራውን በአግባቡ ባልከወነ ቁጥር እኛ በቀጠሮ መጉላላት የለብንም፤ በነጻ ካልሆነም በዋስትና ሊለቀን ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል። ሶስት ጠበቆች ማለትም ፦ 1. ቤተ ማርያም፣ 2. ሰለሞን ገዛኸኝ እና 3. አበበ መስፍን በችሎቱ ተገኝተው ተከራክረዋል። ግንቦት 4/2015 ዓ,ም ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በልደታ ምድብ ችሎት ቀርቦ ከተናገረው መካከልም፦ “በሁከትና ብጥብጥ ጊዜ ሲከሱኝ ምክንያት ገልፀው ነበር፤ እሱን ደግሞ ተከራክረን የ20 ሺህ ብር ዋስትና ተፈቅዶልኝ ከእስር ሳልለቀቅ ድጋሚ በሽብር ክስ ተጠርጥረሀል ተብዬ ፍ/ቤት ቀርቢያለው። እስካሁን ድረስ በእኔ ላይ ምንም አይነት ማስረጃ አላቀረቡም፤ እኔ ለሀገሬ በራሴ ተነሳሽነት ሚዲያ አቋቁሜ እየሰራለሁኝ ባለፉት ሁለት አመታት የነበረውን አሰቃቂ ጦርነት በጥብቅ ስቃወምና ሰላምም እንዲመጣ የበኩሌን ሳደርግ ቆይቻለው። ሰላምም በመምጣቱ ደስተኛ ከነበሩት ዜጎች መካከልም አንዱ ነኝ፤ እኔ በየትኛውም አይነት መልኩ ጦርነትን የምቀሰቅስ አመፅ የማነሳሳ ሰው አይደለሁም። ነገር ግን ዜጎች በሀገራቸው ላይ ጥያቄ ካላቸው በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ማቅረብ ህገ መንግስታዊ መብታቸው ስለሆነ አበረታታለሁ። ከዚህ ውጪ እኔን አሸባሪ የሚያስብል ምክንያት ካላቸው በፍ/ቤት ማሳየት መግለፅ ይችላሉ፤ እኔም እኔ ላይ ያላቸውን ምክንያት በጣም ነው ማወቅ የምፈልገው ያ አለመሆኑ ግን በጣም ሞራሌን እየነካው ነው። ስለዚህ ምንም አይነት ምክንያት ካላቀረቡ ፍ/ቤቱ በነጻ ያሰናብተኝ”። ሲል ለፍ/ቤቱ ስለማስረዳቱ ከቤተሰብ የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ፍ/ቤቱም መዝገቡን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት በሚል ሐከሰዓት በቀጠረው መሰረት 9:30 ላይ ተሰይሟል። ዳኛም በፖሊስ በኩል የቀረበውን መከራከሪያ በመደገፍ ተጠርጣሪ እንጅ ወንጀለኛ ስላልተባሉ በሚዲያ በፎቶ ተደግፎም ቢሆን ቀድሞ መገለጹ ትክክል ነው ብሏል። የምርመራ መዝገቡ ላይ ፍንጭ ስላለ በሚል ፌደራል ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ እና ምስክር ለማሰማት በሚል እንዲሰጠው የጠየቀውን 14 ቀን በመፍቀድ ለግንቦት 18/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply