
ቀጣዩ የትግል መንገድ በትንታኔ እየደረጀ የሚሄድ የፖለቲካ ተዋስኦ ላይ ሊመሰረት ይገባል ❗️ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአብዛኛው አማራ ውስጥ በቂ ቁጣ እና ቁጭት አለ፤ ሆኖም የፖለቲካ ትግል ለማድረግ ከቁጣ ያለፈ ስንቅ ያስፈልጋል። እርሱም ትንታኔ ነው። የሁኔታ፣ የራስ እና የጠላት ትንታኔ ያስፈልጋል። እናም ስለ አማራ ለመታገል እና ለማታገል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በየደረጃው ከዚህ አኳያ ተገቢውን ተግባር ሊፈጽሙ ይገባል። እየደረሰብን ያለውን ግፍ በተመለከተ መረጃ ከማቅረብ እና ከማነሳሳት የሚሻገር ተግባር ከሁሉም አደረጃጀቶች ይጠበቃል። መድረሻን እና ረጅሙን ጉዞ የሚያመላክቱ እንዲሁም መሠረት የሚያስይዙ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥተን እንስራ። ሁሉም አማራ በየአደረጃጀቶች ውስጥ መግባት እና መመርመር፣ ማወቅ፣ መማር እና ማስተማር ይገባዋል። የአደረጃጀቶች መብዛት ለጊዜው ዕድል እንጂ ችግር አይደለም። የጋራ ቅንጅት፣ ህብረት ብሎም በፍጹም የሀሳብ ስምረት እና የአላማ አንድነት ላይ የቆመ የጋራ ቤት ለማቆም <አንድ ሁኑ> በሚል ውሳኔ አይመጣም፤ ይልቁኑ ሁላችንም በየአደረጃጀቶች ውስጥ ገብተን በምንሰራው ስራ በሂደት ወደ ጋራ ሰልፍ ያመጣናል። እናም ህዝብ ወደ አደረጃጀት መግባት አለበት፣ አደረጃጀቶችም ህዝብ ከማነሳሳት የሚሻገር በማያቋርጥ ውይይት ላይ የተመሠረት ትንታኔ እና የመማር መድረኮች መፍጠር ላይ ማተኮር ያስፈልጋል። መድረኮች የግድ የአዳራሽ ውይይት መሆን የለባቸውም እንደየ አውዱ በሚመች መልኩ ሊደረጉ ይገባል። ቁጭት ትግል ይወልዳል እንጂ ትግል አይሆንም፣ ቁጣም ጊዜያዊ መነሳሳት የሚሻገር ስንቅ አይደለም። ምክንያታዊ ትንታኔዎች እና በዚያ ላይ ተመስርቶ የሚያድግ የፖለቲካ ተዋስኦ ሊኖር ይገባል። እናም በቀጣይ ትኩረት ሰጥተን እዚህ ላይ እንስራ። ድል ለአማራ ! #AmharaStruggle #Justice4Amhara #AmharaGenocide “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post