ቀጥታ መልእክት ከክርስትያን ታደለ (የህዝብ እንደራሴ) ለአዳነች አቤቤ (የአዲስ አበባ ከንቲባ)

ሰላም ክብርት ከንቲባ፣   በመጀመሪያ ከተማሪ ወላጆችና ጉዳዩ ካሳሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ከሰሞኑ በከተማችን በተፈጠረው የትምህርት ማኅበረሰብ ችግር ዙሪያ ውይይት ማድረጋችሁን በበጎ የምመለከተው ነው። በመቀጠል ያሉኝን ጥያቄዎች አቀርባለሁ።   አዲስ አበባ የፌዴራሉ መንግስት ዋና ከተማና በሕገመንግስቱ አንቀጽ 49 መሰረት ራሷን ሙሉ በሙሉ የማስተዳደር ነፃነት ያላት ከተማ ነች። ይኼ እውነት በሥራ ላይ ባለው ሕገመንግስት የተቀመጠ ነው። የከተማ አስተዳደሩ የተሻሻለው ቻርተርም ይህንኑ እውነት የሚያስረግጥ ነው። የኦሮሚኛ ቋንቋ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ፍላጎቱ ላላቸው ተማሪዎች መሰጠቱም መጥፎ አይደለም። …

Source: Link to the Post

Leave a Reply