#ቁርጥማት (arthritis)የቁርጥማት ችግር ብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት እና የተለመደ ችግር መሆኑ ይነሳል፡፡በተለይም እድሜያቸው ከ50 አመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ በብዛት እንደሚስተዋል ይነ…

#ቁርጥማት (arthritis)

የቁርጥማት ችግር ብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት እና የተለመደ ችግር መሆኑ ይነሳል፡፡
በተለይም እድሜያቸው ከ50 አመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ በብዛት እንደሚስተዋል ይነገራል፡፡

የተለያዩ አይነት የቁርጥማት አይነቶች መኖራቸውንም የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃም ከ350 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዚህ ህመም የተጠቁ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በዚህ ጉዳይም ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን የዉስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የሩማቶሎጂ ሰብ ስፔሻሊስት ከሆኑት ዶ/ር ብርሀኑ ደመላሽ ጋር ጣቢችን ቆይታ አድርጓል፡፡

#ቁርጥማት (arthritis) ምን ማለት ነው?

ቁርጥማት ማለት የመገጣጠሚዎች ብግነት ወይም ቁጣ ነው ይላሉ ፡፡

#ቁርጥማት በምን #ይከሰታል ?

በዋናነት በሶስት ከፍለን ማየት እንችላለን

– ጫናን ተከትሎ የሚመጣ (degenerative arthritis) በዋናነት ጉልበት እና ዳሌ ላይ የሚከሰት ሲሆን ይህም በብዛት እድሜያቸው የገፉ ሰዎች ላይ፣ ውፍረት ሚያስቸግራቸው ሰዎች ላይ እና ተደጋጋሚ አደጋዎች ሲደርሱ የሚስተዋል ነው፡፡
– ብግነትን ወይም ቁጣን መሰረት አድርጎ የሚመጣ ቁርጥማት (inflammatory arthritis) አይነት በውስጣቸው በዋናነት ሰውነታችን ከራሱ ጋር በሚያደርገው መስተጋብር በሚፈጠሩ ክስተቶች ተከትሎ የሚመጣ ነው ፡፡ በዚህ የቁርጥማት አይነት ላይ ሪህ እንደሚካተትም ይናገራሉ፡፡
– በኢንፌክሽን የሚከሰት የቁርጥማት አይነት በባክቴሪያ እና በሌሎች ምክንያቶች የሚከሰት ነው፡፡

#የቁርጥማት #ምልክቶች ምንድን ናቸው?

ዋና ምልክቶቹ ሶስት መሆናቸውን ባለሙያው ይናገራሉ፡፡
– መገጣጠሚያ ላይ የሚከሰት እብጠት
– ህመም
– ተፈጥሯዊ ቅርፅን ማጣት ናቸው፡፡

#ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች

ለምሳሌ ከሪህጋር ተያዞ የሚመጣ ከሆነ
– የስኳር ህመም
– የግፊት ህመም
– የኩላሊት ችግር
– በጉበት ላይ የስብ መሸፈን ይጠቀስበታል
ከዚህ በተጨማሪም ቆዳን የማጥቃት ባህሪ ሊኖረው እንደሚችልም ይናገራሉ፡፡

#በዋናነት ይህን በሽታ #ለመከላከል

– የሰውነት እንቅስቃሴዎች ማድረግ
– የሰውነት ክብደት መቆጣጠር
– ሲጋራ ማጨስ ማቆም
– የአልኮል መጠጥ መቀነስ እንደሚመረጥ ዶ/ር ብርሀኑ ተናግረዋል፡፡

#ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?

– የደም ምርመራ
– የሰውነት ብግነት መጠኑን ማየት
– ጉበት እንዲሁም ኩላሊቱን ማየት
– ከመገጣጠሚያ ላይ የፈሳሽ ናሙና ወስዶ መመርመር
– አልትራሳውንድ ፣ኤም አር አይ ፣ኤክስሬይ ማየት ይካተቱበታል ይላሉ ባለሙያው

በመጨረሻም ብዙውን ጊዜ የመገጣጠሚያ ህመሞች የረዥም ጊዜ ህክምናዎች የሚጠይቁ በመሆናቸው እና ችግሩን ለመቅረፍም ህክምናው ብቻውን በቂ ስለማይሆን የተመጣጠነ ምግብ መብላት እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ዶ/ር ብርሀኑ ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply