You are currently viewing ቃል -አቫይ  የሆነ ስርዓት የገባውን  ቃል አጥፎ አርበኛ ዘመነ ካሴን አለቀቀውም  ‼️        አሻራ ሚዲያ      መጋቢት 07/2015 ዓ/ም      ባህር ዳር ኢትዮጵያ ቃል -አባይ…

ቃል -አቫይ የሆነ ስርዓት የገባውን ቃል አጥፎ አርበኛ ዘመነ ካሴን አለቀቀውም ‼️ አሻራ ሚዲያ መጋቢት 07/2015 ዓ/ም ባህር ዳር ኢትዮጵያ ቃል -አባይ…

ቃል -አቫይ የሆነ ስርዓት የገባውን ቃል አጥፎ አርበኛ ዘመነ ካሴን አለቀቀውም ‼️ አሻራ ሚዲያ መጋቢት 07/2015 ዓ/ም ባህር ዳር ኢትዮጵያ ቃል -አባይ የሆነ ስርዓት የገባውን ቃል አጥፎ አርበኛ ዘመነ ካሴን አለቀቀውም ‼️ የአማራን ህዝብ እየገዛ የሚገኘው ድርጅት[ ብአዴን ፥አዴፓ] ከሰሞኑ ህዝባዊ ተቀባይነት ለማግኘት የህዝብን ልብ የሚያሞቅ መግለጫ አውጥቶ ነበር ።ነገር ግን ይህንን ያወጣውን መግለጫ የተፃፈበት ቀለም ሳይደርቅ ቃሉን ውጧል፥አጥፏል ። ይህ ቃል -አባይ የሆነ ስርዓት የመላው አማራ ወጣቶች የትግል ምልክት ፣መሪ እና አርዕያ ሆኖ በልባችን የታተመውን አርበኛ ዘመነ ካሴን ለመልቀቅ ወስኖ የነበረ ቢሆንም ቃሉ አጥፎ ፣የወሰነውን ውሳኔ ባለማክበር እስከ ዛሬ ድረስ በሰባታሚት ማረሚያ ቤት በግፍ አስሮ ያሰቃየዋል ። የአማራ ወጣቶች ማህበርም በተለይም የባህር ዳር ቅርንጫፍ አርበኛ ዘመነ ካሴ መንግስት በገባው ቃል መሰረት በአስቸኳይ የማይለቀው ከሆነ ህዝባችን አስተባብረን ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ትግል ፥ እምቢተኝነት የምንጀምር መሆኑን እንገልፃለን ። መላው ህዝባችንም በቀጣይ ለምናደርገው ሁሉን አቀፍ ፤ምልክታችን አርበኛ ዘመነ ካሴን የማስለቀቅ ፤ህዝባዊ ትግልና እምቢተኝነት ራሱን በያለበት እንዲያዘጋጅ የከበረ ጥሪያችን እናስተላልፋለን ። የትግል ምልክታችን ፣መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ልቀቁት ።በማሰር የሚቆም ፥የተጀመረ የአማራ ትግል የለም ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ። ህልውናችን በክንዳችን ነው!!! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply