“ቅርሶቻችን የከፋ አደጋ ላይ ወድቀዋል! ነቅተን ልንታደጋቸው ይገባል!” አቶ ገለታው ዘለቀ የባልደራስ ቢሮ ሀላፊ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም…

“ቅርሶቻችን የከፋ አደጋ ላይ ወድቀዋል! ነቅተን ልንታደጋቸው ይገባል!” አቶ ገለታው ዘለቀ የባልደራስ ቢሮ ሀላፊ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ውስጥ የሚገኘው የደጃዝማች አስፋው ከበደ ቤት በቅርስነት ተመዝግቦ የነበረ ቢሆንም መንግስት ይህንን ታሪካዊ ቤት እንዳፈረሰው ተገልጧል፡፡ የባልደራስ የቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ ከፓርቲው ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ጋር ወደ ቦታው አምርተው ነበር። በቦታው የነበሩ የጥበቃ ሰራተኞችም ወደ ግቢ መግባት እንደማይቻል ገልጸው ጥያቄ ካላችሁ ሂዱና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠይቁ ብለው እንደመለሷቸው ተጠቅሷል፡፡ ባልደራስ ይህንን ጉዳይ በጥብቅ የሚከታተል ይሆናል ያሉት የባልደራስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ የሀገራችንን ቅርስ እያፈረሱ ያሉ አካላት በህግ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ በቅርስነት የተመዘገበው የደጃዝማች ቤት ሲፈርስ የቅርስ ባለሙያዎች ወደ ቦታው በመሄድ ቅርስ ነው አታፍርሱ እያሉ ለመከላከል ቢሞክሩም በወታደር እንደተባረሩ መረጃ ደርሶናል ብሏል ባልደራስ። ፅንፈኞች የታሪክ አሻራዎቻችንን ለማጥፋት ተነስተዋልና መላው ህዝባችን ቅርሶቹን ለመጠበቅ በጋራ መነሳት አለበት ሲሉ አቶ ገለታው ዘለቀ ስለመናገራቸው ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply