ቅዱስ ሲኖዶስ በመንግስት የጸጥታ መዋቅር ቸልተኝነት በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየደረሰ ስላለው ጥቃት ከመንግስት ጋር በግንባር የሚወያዩ 12 አባላት ያሉት የብፁዓን አባቶች ልዑክ አዋቀረ። አማራ…

ቅዱስ ሲኖዶስ በመንግስት የጸጥታ መዋቅር ቸልተኝነት በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየደረሰ ስላለው ጥቃት ከመንግስት ጋር በግንባር የሚወያዩ 12 አባላት ያሉት የብፁዓን አባቶች ልዑክ አዋቀረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንግስት የጸጥታ መዋቅር ቸልተኝነት በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየደረሰ ስላለው ጥቃት ከመንግስት ጋር በግንባር የሚወያዩ 12 አባላት ያሉት የብፁዓን አባቶች ልዑክ አዋቀረ። የተሰየመው ልዑክ 12 ብፁዓን አባቶችን የያዘ ሲሆን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩም እንደሚገኙበት ተጠቁሟል። ኮሚቴው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በግንባር ቀርቦ የሚወያይ ሲሆን በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየደረሰ ስለሚገኘው ሃይማኖት ተኮር ጥቃት እንደሚወያይ ይጠበቃል። በተጨማሪም በሀገራዊ ጉዳይ ላይ በመንግስትና በአንዳንድ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ስለተፈጠረው አለመግባባትም ጉዳዩ በውይይት እንዲፈታ ለማድረግ ልዑካንን መሰየሙ ተጠቁሟል። በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት እንደተከናወነው ሁሉ በየአህጉረ ስብከቱ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን የህግ ባለሙያዎች በመተባበር ህገወጦችን በህግ ሊፋረዱ እንደሚገባ ተገልጿል ያለው የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply