ቅዱስ ሲኖዶስ: በቆጋ ገዳም የተፈጸመውን ኢቀኖናዊ እና ኢሕጋዊ የጵጵስና እና የፕትርክና ሹመት ሻረ፤ እጃቸውን ያስገቡ ባዕዳን እንዲቆጠቡ አሳሰበ

ቅዱስ ሲኖዶስ: በቆጋ ገዳም የተፈጸመውን ኢቀኖናዊ እና ኢሕጋዊ የጵጵስና እና የፕትርክና ሹመት ሻረ፤ እጃቸውን ያስገቡ ባዕዳን እንዲቆጠቡ አሳሰበ

https://1.gravatar.com/avatar/7f09202441ad3b4b636e88820d6a7061?s=96&d=identicon&r=G
  • የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ እና ሕግን በመተላለፍ፣ ራሳቸውን በራሳቸው የሾሙ መነኰሳት፣ በቀኖና እንዲቀጡ ወሰነ፤ የቅስና ሥልጣናቸው እና ማዕርገ ምንኵስናቸው ተጠብቆላቸዋል፤
  • “ኮሚቴ ነን” እያሉ የተወገዘውን የቅብዐት እምነትን በቤተ ክርስቲያናችን ይዞታ እና ንብረት ለማደራጀት የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች፣ ከሕገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ፤
  • ፕሮቴስታንታውያንና የተሐድሶ መናፍቃን፣ በገንዘብም ጭምር እንደሚደግፉት በማስረጃ በመረጋገጡ፣ ከጣልቃ ገብነት እጃቸውን እንዲሰበስቡ አስጠነቀቀ፤
  • በአንዲት ቤተ ክርስቲያን በአንድ ሃይማኖት እና በአንድ ካህን የምትፈጸመው ጥምቀት አንዲት በመኾኗ፣ “ዳግም ጥምቀት” በሚል የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዲቆም አዘዘ፤
  • ሀገረ ስብከቱ፣ ኦርቶዶክሳዊውን የነገረ ክርስቶስ(ነገረ ሥጋዌ) አስተምህሮ፣ በልዩ እና ተከታታይ የስብከተ ወንጌል ጉባኤያት እንዲሁም የትምህርተ ወንጌል እና የሥልጠና መርሐ ግብሮች እንዲያጠናክር እና እንዲያጸና መመሪያ ሰጠ፤
  • ሕገ ወጦቹን ተሿሚዎች እና ግብረ አበሮቻቸውን በማጋለጥ እና በመቆጣጠር ትብብር ያደረጉ፣ የሀገረ ስብከቱን አድባራት እና ገዳማት፣ ምእመናንና የመንግሥት አካላትን አመሰገነ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply