
ቅዱስ ሲኖዶስ በክህደት ተግባሩ ያወገዘውን ቡድን በትጥቅ እያጀበ ወደተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እያስገባ ያለው አገዛዙ የተዋህዶ ልጆችን ማሰሩን ቀጥሎበታል ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ቅዱስ ሲኖዶስ በክህደት ተግባሩ ያወገዘውን ቡድን በትጥቅ እያጀበ ወደተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በኃይል እያስገባ እና ተኩሶም እየገደለ ያለው የአብይ አህመድ የኦሮሙማ አገዛዝ የተዋህዶ ልጆችን እያሳደደ ማሰሩን ቀጥሎበታል ሲሉ አሚማ ያነጋገራቸው ምንጮች ተናግረዋል። ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሳሳቢነቱ ቀጥሏል የሚሉት ምንጮች በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የየካቲት 5ቱ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ በማሰብ የአፈና እና የእስር ተግባሩን አጠናክሮ ስለመቀጠሉ ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት:_ 1) ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ፌቨን ዘሪሁን እንዲሁም 2) ዋና ፀሐፊዋ ወጣት ብሩክታዊት መታሰራቸውን ተሚማ አረጋግጧል።
Source: Link to the Post