ቅዱስ ሲኖዶስ: ዐዲስ አበባን “ልዩ ሀገረ ስብከት” ያደረገው ሕግ እንዲሻሻል በአብላጫ ድምፅ ወሰነ፤ ቅዱስነታቸው ማሻሻያውን ተቃወሙ

https://1.gravatar.com/avatar/7f09202441ad3b4b636e88820d6a7061?s=96&d=identicon&r=G
  • በማሻሻያ ውሳኔው መሠረት፣ ዐዲስ አበባ እንደማንኛውም ሀገረ ስብከት፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ በሚመድበው ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ይመራል፤
  • ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት በሦስት ብፁዓን አባቶች ተጠቁመው እና ሀገረ ስብከቱን ለመምራት ባላቸው ብቃት ተወዳድረው በብዙኀኑ የተመረጠው ብፁዕ አባት በምልአተ ጉባኤው ይመደባል፤
  • “የልዩ ሀገረ ስብከት” ድንጋጌ የአማሳኞች መጠቀሚያ እንጂ፣ የገዘፉ የመዋቅር፣ የአደረጃጀት እና የአሠራር ችግሮቹን ለማረም አመቺ ባለመኾኑ፣ በሓላፊነት የሚጠየቅ አንድ ሊቀ ጳጳስ በውድድር ያለጣልቃገብነት መመደብ ማስፈለጉ ተገልጿል፤
  • ቅዱስነታቸው በበኩላቸው፣ ምልአተ ጉባኤው ድንጋጌውን የማሻሻል ሥልጣን እንዳለው ቢያምኑም፣ ማሻሻያውን ለማድረግ የሚያበቃ አሳማኝ ምክንያትና በሌሎች አህጉረ ስብከት ከሚታየው የተለየ የተጠና ችግር እንዳልቀረበላቸው በመግለጽ ሐሳቡን አክርረው በመቃወማቸው በልዩነት ተወስኗል፤
  • አጀንዳው የተያዘው፣ “ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሙሉ እንዲሻሻል ማድረግ” በሚል ቢኾንም፣ የዐዲስ አበባን “የልዩ ሀገረ ስብከት ድንጋጌ” ብቻ፣ ኹለት ቀናት በፈጀ የተካረረ ውይይት በማሻሻል፣ ከቀትር በኋላ በቀሪዎቹ አጀንዳዎች መወያየቱን እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply