ቅድመ ማስጠንቀቂያ ————- ሸንቁጥ አየለ ———— አቢይ አህመድ  ዜጎችን ከሞት ከመጠበቅ ይልቅ የዘር ፍጅት አከናዉኖ ሬሳን በነገድ አደላዳይ መሪ ነዉ::… —…

ቅድመ ማስጠንቀቂያ ————- ሸንቁጥ አየለ ———— አቢይ አህመድ ዜጎችን ከሞት ከመጠበቅ ይልቅ የዘር ፍጅት አከናዉኖ ሬሳን በነገድ አደላዳይ መሪ ነዉ::… —…

ቅድመ ማስጠንቀቂያ ————- ሸንቁጥ አየለ ———— አቢይ አህመድ ዜጎችን ከሞት ከመጠበቅ ይልቅ የዘር ፍጅት አከናዉኖ ሬሳን በነገድ አደላዳይ መሪ ነዉ::… —————- 1– አቢይ ሀገር መምራት አይችልም ብቻ ሳይሆን ሀገር ምንድን ነዉ የሚለዉን ያልተረዳ ሰዉ ነዉ::በፍጥነት ስልጣኑን መልቀቅ ያለበት ለመሪነት እራሱን ያላበቃ ሰዉ:: 2-አቢይ ልቡ ክፉ ነው: ጸረ አማራ ነዉ:ጸረ ኦርቶዶክስ ነዉ:ጸረ ኢትዮጵያዊ ነው::ልቡ ክፉ ስለሆነም ይሄ ሁሉ ህዝብ ሲያልቅ የሀዘን መግለጫ እንኳን የማይናገር ሰዉ ነዉ:: 3. አቢይ ልቡ ክፉ ብቻ ሳይሆን እጅግ ጥልቅ የዘረኝነት በሽታ ህሊናዉን የተቆጣጠረዉ ሰዉ ነዉ::አንድ አጫሉ ሞተ ብሎ መቶ ሰላሳ ጊዜ በዬሚዲያዉ እየወጣ ሲያላዝን የነበረ ሰዉ በብዙ አስር ሽህ ዜጎች ሲጨፈጨፉ:የዘር ፍጅት ሲደረግባቸዉ:ሲፈናቀሉ ግን አንድም ጊዜ አንዲትም ቃል ለመናገር የሚጸዬፍ ታላቁ የክፍለ ዘመናችን ዘረኛ ነዉ:: 4–አቢይ ስልጣን ሳያስበዉ እጁ ቢገባም ስልጣንኑ በህዝብ ደም አስጠብቆ መቀጠል የሚመስለዉ ሞኝ ነዉ 5.አቢይ አማራን የሚያህል የሀገሪቱን ትልቁን ነገድ ጨፍጭፎ ማጥፋት የሚችል የሚመስለዉ የኦነጋዉያን የሞኝነት ስሌት ተሸካሚ ነዉ 6- አቢይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የሚያህል የሀገሪቱን ቁጥር አንድ ብዛት ያለዉን እምነት ለማጥፋት ብዙ ዉስብስብ መንገዶችን የተከተለ ሰዉ ነዉ 7-አቢይ የኮንሶን:የጌዲዮን:የጋሞን እና ልዩ ልዩ የኢትዮጵያን አነስተኛ ቁጥር ያላቸዉን ነገዶች ጨፍጭፎ ለማጥፋት ኦነግ ሸኔን በመሳሪያነት እየተጠቀመ ያለ ነዉ 8- አቢይ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ በጣም የናቀ: የኢትዮጵያን ህዝብ በጣም የናቀ እና በራሱ እብሪተኛ አለም ብቻ የሚሽከረከር ሰዉ ነዉ 9-አቢይ በመጨረሻም በአለም አቀፍ የወንጀለኛ ፍርድ በዘር ማጽዳት እና ማጥፋት ወንጀል ተከሶ እድሜ ልክ እስራት የሚፈረድበት ሰዉ ነዉ:: 10- አቢይ እዉነት እና ማስመሰል የተምታቱበት ሰዉ ነዉ:: 11- አቢይ ሻሸመኔ ከተማ እንዳለ ሲወድም:በአንድ ቀን በኦሮሚያ ሃያ ሽህ ህዝብ የዘር ፍጅት ሲደረግበት:በአንድ ቀን በጀዋር ተከበኩ 300 ህዝብ ሲጨፈቸፍ:በቤኒሻንጉል በሶስት ተከታታይ ቀናት ብቻ ከሽህ ህዝብ በላይ ተጨፍጭፎ በግሬደር የህዝብ እሬሳ እንደ ቆሻሻ ሲሰበሰብ ለአቢይ እነዚህ ሰዎች ከሱ ነገድ ስላልሆኑ ሰዎች አይደሉም::ሆኖም አቢይ ማስመሰል እና እዉነት የተምታታበት ሰዉ ነዉና ነገ ብቅ ብሎ ሳይፍር እሬሳ በነገድ እየደለደለ ከዚህ ነገድ ያን ያህል: ከዚያኛዉ ያን ያህል የሚል ድርሰት ይጽፋል::ሁሉም ሞቷል ለማለት መሆኑ ነዉ::የሱ ስራ ግን በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የሚገኝ ኢትዮጵያዊም ሆነ ወይም ኢትዮጵያዊም አልሆነ ሰዉ የሆነ ሁሉ እንዳይገደል ማድረግ መሆኑን ፈጽሞ የማያዉቅ ሰዉ ነዉ::ስራዉን የማያዉቅ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነዉ::ወይም ደግሞ ስራዉን በቅንነት ለመፈጸም ልቡ በጥላቻ:በክፋት:በዘረኝነት:በክፉ መንፈስ የጠቆረ ሰዉ ነዉ::የሰዉ ልጅ ህይወት ከጫጩትም ህይወት ያነሰ ሆኖ የሚሰማዉ ልበ ጩቤ አፈ ቅቤ ሰዉ ነዉ:: 12.የአቢይ ደጋፊዎችም ልክ እንደ አቢይ ለሚጨፈጨፈዉ ህዝብ ከማዘን ይልቅ ልባቸዉን በማጠጠር እና በማጨከን ምንም አዲስ ነገር የለም ይሄ ነገር በደርግም በሀይለስላሴም ጊዜ ይደረገ ነበር ብለዉ የሚከራከሩ ናቸዉ::ነገ በኛ ላይስ ቢደረግ ብለዉ ግን ቆመዉ ለማሰብ ፈቃደኝነት ይጎላቸዋል::ልክ የወያኔ ደጋፊዎች አይናቸዉን ጨፍነዉ የወያኔን ሀጢያት ሁሉ ሲከራከሩለት እንደነበረዉ ብቻ ሳይሆን የአቢይ ደጋፊዎች ደግሞ ከወያኔ ደጋፊዎች በባሰ ዘረኝነት አይናቸዉን ጨፍነዉ ወንጀልን እና ወንጀለኛን በመደገፍ ላይ ናቸዉ:: ከእናንተ ነገድ ስለሆነ:ከእናንተ ሀይማኖት ስለሆነ:ከብልጽግና ፓርቲ ስለሆነ ወይም በሌላ ምክንያት አቢይን የምትደግፉ አቢይ በሚፈጥረዉ የወንጀል ዳፋ ብዙ ሀገራዊ ጥፋት እንደሚመጣ እወቁ::ወንጀሉም ተንከባላይ እና ሁሉንም የሀገሪቱ ክፍል እና ማህበረሰብ ዋጋ የሚያስከፍል እንጅ እንዱን ነገድ በልቶ ሌላዉ የሚተርፍ አይሆንም::ስለሆነም አቢይ በስልጣን አይነ ልቦናዉ ቢታወርም እናንተ ግን ቆም ብላችሁ የምትደግፉትን ሰዉ ብትገስጹት ይበጀዋል እንጂ ህዝብ በጅምላ እያስጨረሰ አሁንም በጭፍን ብትደግፉት እናንተንም ዋጋ እንደሚያስከፍላችሁ እወቁ:: ቅድመ ማስጠንቀቂያ መሆኑ ነዉ:: ይሄ ጽሁፍ ነገ የምንጠያዬቅበት ቅድመ ማስጠንቀቂያ መሆኑ ነዉ::ልክ ክፉ ቀን ሲመጣ ያኔ ይሄን ብታስጠነቅቁን ኖሮ እንዳትሉ ዛሬ በዲሴምበር 26/2020 ይሄን ማስታወሻ ለሚመለከተዉ ሁሉ ጽፌላችኋለሁ:: አሁን ስራዬ መጻፍ ነዉ::እዉነት የሆነዉን ነገር መጻፍ ነዉ:: እዉነቱም በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል አሸናፊም ተሸናፊም የለም::ኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን/እነ አቢይ እንደሚያስቡት ያሸነፋችሁት ወገን የለም:: አማራን አሸነፍነዉ ብላችሁ አትጨፍሩ::ልክ እንደ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የማይጨበጥ : የማይማረክ እና የማይሸነፍ ጽኑ መንፈስ ያለዉ አንዴ ከተነሳም ያጠቁትን ጠላቶቹን ሁሉ የመብላት ጉልበት ያለዉ ህዝብ ነዉና አማራን በመጨፍጨፍ የምታጠፉት እንዳይመስላችሁ::የሚሻላችሁ አማራዉንም ሆነ ልዩ ልዩ ኢትዮጵያዉያንን በፍቅር እና በአንድነት መምራት ነዉ::እግዚአብሄር ስልጣንን እጃችሁ ላይ ያስገባዉ ፍትህ እንድትሰሩ እንጂ አማራዉን እና ልዩ ልዩ ነገዶችን እንድታጠፉ እንዳልሆነ እወቁ:: ኢትዮጵያም የሚከፋፈል ሀገር አይደለም:: ኢትዮጵያ የማይከፋፈል ሀገር የሆነዉ ማንም ጀግና ጠብቆት አይደለም::እናንተ ባታምኑበትም እግዚአብሄር በመጽሃፍ ቅዱስ ህዝቤ የሚለዉን ቃል ለኢትዮጵያዊ ሰጥቷል እና ይሄ ቃል አይሻርም::ኦነጋዉያን/ኦህደዳዉያን ይሄን መለኮታዊ ቃል ተረት ተረት እንደምትሉት በደንብ አዉቃለሁ::ግን ይሄ ነገር ሲሆን ቆማችሁ በመከራ ዉስጥ እያለቀሳችሁ ታዩታላችሁ እና በልባችሁ የእግዚአብሄርን ስራ በመጨረሻዉ ሰዓት ብታስተዉሉት ብዬ ይሄን ቅድመ መረጃ እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጻፍኩላችሁ:: ዛሬ በሚሰራዉ ወንጀል የተነሳ ግን እጅግ መራራ እዳ እና እልቂት ዛሬ ወንጀል በሚፈጽሙም በሚያስፈጽሙም በዝምታ ተባባሪ በሆናችሁም ላይ ይመጣል እና እዳዉ ብሎም ዳፋዉ መሰረቱ ጥልቅ ነዉ::ለዚህም ነዉ ዛሬ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጋራ ቆሞ ዘሬ ሀይማኖቴን ሳይል በአንድ ድምጽ ወንጀልን እና ወንጀለኝነትን መቃወም ያለበት:: እናም ይሄ ጽሁፍ በአቢይ የወንጀል ዳፋ የሚመጣዉን እዳና መከራ ሁሉ ቀድሞ የሚያስጠነቅቅ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ነዉ::ያዉ ከእኔ እንዲወጣልኝ እንጂ ከአቢይ ደጋፊዎች መሃከል ማንም የሚያምነኝ ወይም ሰምቶ የሚተገብረዉ እንደማይኖርም በደንብ አዉቃለሁ::ሆኖም ቅድመ ማስጠንቀቂያዉን የመጻፍ ግዴታ ስላለብኝ ይሄን መልዕክት አስተላልፌላችኋለሁ:: ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይጠብቃት !

Source: Link to the Post

Leave a Reply