ቅ/ሲኖዶስ የብፁዓን አባቶች ዝውውር እና ምደባ አደረገ፤ ብፁዕ አባ ማርቆስ ከኒውዮርክ ወደ ደብረ ማርቆስ መመለሳቸው ምልአተ ጉባኤውን እያነጋገረ ነው

ቅ/ሲኖዶስ የብፁዓን አባቶች ዝውውር እና ምደባ አደረገ፤ ብፁዕ አባ ማርቆስ ከኒውዮርክ ወደ ደብረ ማርቆስ መመለሳቸው ምልአተ ጉባኤውን እያነጋገረ ነው

https://1.gravatar.com/avatar/7f09202441ad3b4b636e88820d6a7061?s=96&d=identicon&r=G

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ በዛሬ ቅዳሜ፣ ጥቅምት 21 ቀን የቀትር በፊት ውሎው፣ የአራት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ዝውውር እና ምደባ አድርጓል፡፡ በዚኽም መሠረት፡-

  1. የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ በፈቃዳቸው ለመዛወር ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ ወደ ሲዳማ ጌዲዮ እና ቡርጂ ዞኖች አህጉረ ስብከት(ሓዋሳ) ተዛውረዋል፤ በእርግና እና የጤና እክል ያሉት የሲዳማ ጌዲዮ እና ቡርጂ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ደግሞ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ማረፊያቸው በጸሎት ተወስነው ረዳት እንዲመድብላቸው ወስኗል፡፡
  2. የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ ቀድሞ ወደነበሩበት ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ተዛውረው እንዲሠሩ እና የምሥራቅ አውስትራልያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ኒውዮርክ ሀገረ ስብከት እንዲዛወሩ ወስኗል፡፡ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት፥ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ ከአስተዳደራዊ ችግር ጋራ በተያያዘ በከፍተኛ እና ተደጋጋሚ የሕዝብ ተቃውሞ የተነሡበት እንደነበር እየታወቀ በዝውውር ተመልሰው እንዲመደቡ መደረጉ፣ “ሁከቱን ዳግም ይቀሰቅሰዋል፤” በሚል የምልአተ ጉባኤውን አባላት እያነጋገረ ነው፤ ቅዱስ ፓትርያርኩም ጭምር፣ “ይኼ ነገር ችግር ያመጣል፤” ብለው ስጋታቸውን ቢገልጹም፣ የብፁዕ አባ ማርቆስን መመለስ የሚደግፉ ብፁዓን አባቶች ቡድን፣ “ሀገረ ስብከቱን ቀድሞም ያውቁታል፤ ሰላም ያደርጉታል፤ ያለሙታል፤” በማለት ግፊት በማድረጋቸው፣ ማሳሰቢያው ሰሚ አጥቶ ዝውውሩ መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡

3. የምዕራብ አውስትራልያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ፣ ሀገረ ስብከታቸውን እንደያዙ የምሥራቅ አውስትራልያ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ ተመድበዋል፡፡

4. ባለፈው ዓመት ባረፉት የዩናይትድ ኪንግደም እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ሣልስ ምትክ፣ የሩቅ ምሥራቅ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ ሀገረ ስብከታቸውን እንደያዙ ደርበው እንዲሠሩ ተመድበዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply