ቆቦ ውስጥ ስድስት መቶ ሰው እንደተገደለ ነዋሪዎች ተናገሩ

https://gdb.voanews.com/BF762538-4979-41D0-95A7-E875E7FFE725_cx0_cy10_cw0_w800_h450.jpg

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀው የህወሓት ታጣቂዎቹ በሰሜን ወሎ በቆቦ ከተማና አካባቢው ከ6 መቶ በላይ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን እና ሌሎች አስከፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችም ፈጽመዋል ሲሉ የድርጊቱ ሰለባዎች መሆናቸው የተናገሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ገለፁ።

ጉዳዩን አስመልክቶ መረጃ ያለው መሆኑን የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ ሁኔታው በእጅጉ እንዳሳሰበው አስታወቀ። እጅግ የበዛ ሰውም ከአካባቢው እንደተፈናቀለ የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። 

በጉዳዩ ላይ ከህወሓት ወገን እስካሁን የተገኘ ቀጥተኛ ምላሽ የለም። ሆኖም ክልሉን በመምራት የሚገኙት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ድርጅታቸው

“የትግራይ መከላከያ ኃይሎች” በሚል የሚጠራቸው ታጣቂዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ እንዲህ ያሉ ድርጊቶችን እንደማይፈፅም ገልፀው፤ በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡባቸው ውንጀላዎች በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩላቸው ጠይቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply