ቆይታ፦ ከስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን አማካሪ ቤርናር ላውራንዱ ጋር

https://gdb.voanews.com/89541CEC-CD5D-4076-91E8-6C6886AD156C_w800_h450.jpg

 በአውሮፓዊያኑ 2030 ዓመተ ምህረት ለዜጎቿ 20 ሚሊየን  አዳዲስ ስራዎቿን ለመፍጠር ያቀደቸው ኢትዮጵያ፣ ካለመችበት ለመድረስ የተለያዩ መርሀ-ግብሮች በመተግበር ትገኛለች።

ከእነዚህ መካከል በሳይንስ ፣ቴክኖሎጂ ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ ትምህርቶች (STEM) በየዓመቱ የሚመረቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ለእንጀራ ያበቃል ብላ ተስፋ የጣለችበት በእንግሊዝኛ ምህጻሩ፣ FROG የተሰኘው መርሀ ግብር ይገኛል።

Freelancing, outsourcing and Gigs የሚሉ ቃላትን ያቀናጀው አሰራር ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ጥራት ያለው አገልግሎት በተሻለ ዋጋ  ከሚፈልጉ ሀገራት ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ተቋማት ስራዎችን በተለያየ የውል ግንኙነት አማካኝነት ተረክበው የሚሰሩበት ዓይነት ነው።

ህንድን በመሰሉ ሀገራት የተለመደው አሰራር ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ቢተገበር የዲጂታል ኢኮኖሚውን የማነቃቃት ፣ ለበርካቶች ስራ የመፍጠር አቅም አለው ብሎ ያመነው የኢትዮጵያ የስራ ዕድል ኮሚሽን ተዛማች ስራዎችን ከጀመረ ሰነባብቷል።

ስለ መርሐ-ግብሩ ለማወቅ እና ተያይዘው ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ሀብታሙ ስዩም ወደ አቶ ቤርናር ላውራንዱ ደውሏል። አቶ ቤርናር ከ10 ዓመት ለተሻገረ ጊዜ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የዲጂታል ስርዓትን በተመለከተ አማካሪ ሆነው ሰርተዋል። በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን በከፍተኛ አማካሪነት እያገለገሉ ይገኛሉ።

አስቀድመው ኢትዮጵያ ከሌሎች ዘርፎች በተለየ ዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ ማተኮር ለምን እንዳስፈለጋት ያስረዳሉ፦

 

Source: Link to the Post

This Post Has 2 Comments

  1. Missa Yitbarek

    Good Information

  2. Missa Yitbarek

    I have got good a Information about Covid 19 Vaccination.

Leave a Reply