የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዮት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ሰርጀቦ እንደገለፁት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ መከሰቱን ተከትሎ የቆዳና የቆዳ ውጤቶችን በሚፈለገው ደረጃ ወደ ውጭ ሀገራት ለመላክ ባለመቻሉ የጥሬና የቆዳ መሸጫ ዋጋ ሊቀንስ እንደቻለ ተናገረዋል፡፡
ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፊት የቆዳ መሸጫ ዋጋ ለመቀነሱ ምክንያቱ የቻይና እና የአሜሪካ የእርስ በርስ የንግድ ጦርነት እንደነበረ ጠቁመዋል፡፡ጥሬ ቆዳ፣ ለቆዳ ኢንዱስትሪዎች የስራ እድል የሚፈጥር በመሆኑ እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ተስፋ ስለሚኖረው ህብረተሰቡ ቆዳዎችን በጥንቃቄ ለገበያ በማቅረብ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡየኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዮት አሳሰበ፡፡
**************************************************************************
ቀን 27/04/2013
አሐዱ ራዲዮ 94.3
Source: Link to the Post