በሀረሪ ክልል ያለው ንጹህ የመጠጥ ውኃ እጥረት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ተባለበክልሉ ያለው የንጹህ መጠጥ ውኃ እጥረት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆኑን የሀረሪ ክልል ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን አስ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/CupHbfQnCLsZoYLMLux7DqufnzdHSFYrwkMRo0M8vkgPjFAoiVVMvcmXOI1x5R1vx7vQ4YDVClF8QvsBttfARzbD3ojuIghv9D8dTLUxVpaqmFdn074nGMjl4vNB3Uk0or4xUY870SurcWMU69h6MusgeUXqqHEMPnCastjhjYm1IDH5dETuFNARut6phYltXLnG7MeS3qGVbfo4UoEBFJxK6TLN8YA5elTLEoqYuR7IBaTjrr9A9EV0CUkKvc7afJV8OkTcH5cBAjE3tcvpHoZYggA2vCf-Iq_4i8bey5HgHdLNC0s89wAFpU3K-2XyhHNT46icEHqxV2zl5tetJg.jpg

በሀረሪ ክልል ያለው ንጹህ የመጠጥ ውኃ እጥረት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ተባለ

በክልሉ ያለው የንጹህ መጠጥ ውኃ እጥረት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆኑን የሀረሪ ክልል ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

በውሃ እጥረቱ ህጻናት እና አቅመ ደካሞች በከፍተኛ ሁኔታ መቸገራቸው የሚገሩት የሀረሪ ክልል ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሚኒኬሽን ሀላፊ አሪፍ ጠሃ ናቸው።

ከድሬደዋ ከተማ 72 ኪሎ ሜትር አሰሊሶ እና ሁላሀሉል መንደሮች ውሃ ለማምጣት ጥረቶች መደረጋቸውን የገለፁ ሲሆን  የቦታው እርቀት እስቸጋሪ ሆኗል ተብሏል፡፡

በክልሉ ያለው የውሃ እጥረት ከንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት በተጨማሪም የመብራት መቆራረጥ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡ በመሆኑም ንጹ የመጠጥ ውሃ ለህብተሰቡ በቦቴ እየተከፋፈለ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

በክልሉ ያለውን የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረትን ለመቅረፍ አንድ ጄሪካን በ5 ብር እየከፈሉ ህብረተሰቡ እንዲጠቀም መደረጉን ተመላክቷል፡፡

ነገር ግን በባለስልጣኑ ከተተመነው ተመን ውጪ የሚያስከፍሉ የመጠጥ ውኃ አከፋፋዮች  ላይ ቁጥጥር ይደረጋል ተብሏል፡፡

በክልሉ ያለው የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ ጥናቶች መከናወናቸውን ተጠቁሟል ፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply