በሀረሪ ክልል ያለው የሆቴል እጥረት በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ተግዳሮት ሆኗል ተባለበክልሉ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች ቁጥር 10 እንደማይሞሉ ተነግሯል፡፡የሀረሪ ክልል በዘጠኝ ውስጥ ከቱሪዝም ዘርፍ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/uGH_uiQiQWPi33S2KsB3fMKGXi3NxcqvCTI7659Vi_ylC7ac62AYTZ8BGhIomTFroZCC9rEuYRBF0WYj0YvFJ3VZ39S5nKPUxAEQYmW-FzA_oW7ls1Ii0lPxjcCw3EPJApLCx-ywzOcqXSiktZPGLSU_82-I15WS6goQurJhYhH_8FVfo0s1a6t-gT7Y7sqFj6R4jK6k01hVPWy29JOVJ8JWTsndA3MWp-LWZjjEWMDJ01DJVd09gTwNB3Xa5qhWvIgP8WwcnFN8rlmkWhLovQNUqjf35wqRtKfZASz_M3B7JvzZShg28TJabi9U1m7snCk0B1UxQNHQzpNMutG9pQ.jpg

በሀረሪ ክልል ያለው የሆቴል እጥረት በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ተግዳሮት ሆኗል ተባለ

በክልሉ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች ቁጥር 10 እንደማይሞሉ ተነግሯል፡፡

የሀረሪ ክልል በዘጠኝ ውስጥ ከቱሪዝም ዘርፍ ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ የነገሩን፤ የሃረሪ ክልል ቅርስ እና ቱሪዚም ቢሮ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሳሚ አብዱልዋሲ ናቸው፡፡

ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች ክልሉን ምቹ ለማድረግ ከ55 በላይ መንገዶች እድሳቶች ተከናውነዋል ተብሏል፡፡ በክልሉ ያለው የሆቴል እጥረት ግን ለቱሪዝሙ ዘርፍ ተግዳሮት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ክልሉ 50 በመቶ የሚሆነው ገቢው ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኝ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ፤ በዘርፉ ላይ ትኩረት በመስጠት ለጎብኘኚዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

ባለፉት 9 ወራት ከ4 ሺ 300 የሚሆኑ የውጭ ሀገር ጎብኝዎችን ለማስጎብኘት በእቅድ የተያዘ ሲሆን፤ ከ5 ሺህ በላይ ጎብኝዎች ወደ ክልሉ መምጣታቸው ተገልቷል፡፡ እንዲሁም ከ1 መቶ 22 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ከክልሉን መጎብኘታቸው ተነግሯል፡፡

ከዓምናው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የጎብኚዎች እንዲሁም በገቢ ደረጃ መሻሻሎች መስተዋሉ ተገልጻል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply