በሀረር ከተማ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካና የመላው ጥቁር ህዝብ ባለውለታ የሆኑትን የእምዬ ምኒልክ ምስል ያለበት ቲሸርት አሰራጭተሃል ተብሎ ሲቪል በለበሱ 2 የደህንነት አካላትና በፖሊስ ለ3…

በሀረር ከተማ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካና የመላው ጥቁር ህዝብ ባለውለታ የሆኑትን የእምዬ ምኒልክ ምስል ያለበት ቲሸርት አሰራጭተሃል ተብሎ ሲቪል በለበሱ 2 የደህንነት አካላትና በፖሊስ ለ3…

በሀረር ከተማ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካና የመላው ጥቁር ህዝብ ባለውለታ የሆኑትን የእምዬ ምኒልክ ምስል ያለበት ቲሸርት አሰራጭተሃል ተብሎ ሲቪል በለበሱ 2 የደህንነት አካላትና በፖሊስ ለ3 ቀናት ታስሮ የሰነበተው የአብን እጩ ተፈታ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በእለተ ቅዳሜ የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ረፋድ ላይ የኢትዮጵያ፣የአፍሪካና የመላው ጥቁር ህዝብ ባለውለታ የሆኑትን የእምዬ ምኒልክ ምስል ያለበት ቲሸርት አሰራጭተሃል በሚል የታሰረው የአሽከርካሪዎች አሰልጣኝ ሄኖክ ኃይሉ ስለመታሰሩ ጃኖ የሐረር ልጆች ጥምረትን ዋቢ በማድረግ የአማራ ሚዲያ ማዕከል መዘገቡ ይታወሳል። ከ3 ቀናት የእስር ቆይታ በኋላ የተፈታውን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ እጩ ተወዳዳሪ ሄኖክ ኃይሉን በቀጥታ የስልክ መስመር አግኝተን አነጋግረነዋል። ሄኖክ እንደሚለው ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግስት ደረጃ የአድዋ በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረነው፤ መንፈሱም ጥሩ ነው በሚል እምነት የእምዬ ምኒልክ፣የእቴጌ ጣይቱና የባልቻ ምስል ያለበት ቲሸርትን በመልበስ ከድሬድዋ የተላከለትን ቲሸርት ለሚፈልጉ ወንድም እና እህቶች ለማድረስ ገና ከመኪና ሲቀበል ነው ክትትል ሲያደርጉ በቆዩና መሳሪያ በደገኑ በሁለት ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላትና በአንድ የሀረር ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል። በሀረር ፖሊስ መምሪያ ታስሮ የቆየው ሄኖክ ቀደም ሲል በሐረር ፍትህና ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ውስጥ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ገልጾ ምርጫ ቦርድ ፓርቲውን መሰረዙን ተከትሎ ግን ፓርቲ ከአብን የተለዬ አላማ የሌለው በመሆኑ ከሀረር ጀጎል ውጭ የፓርቲው እጩ በመሆን እየታገሉ መሆኑን አስታውቋል። አብን ከሀረር ጀጎል ውጭ በ6 ወረዳዎች እንደሚወዳደር ነው ሄኖክ ጨምሮ ያስረዳው። ከአሳሪዎች መካከልም በሀረር የአቦካ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበረው አቶ ሱልጣን ሳሚ እንደሚገኝበት አስታውቋል። ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በአደራ መልክ ታስሮ ለ3 ቀናት የቆየው ሄኖክ ቲሸርቱን ከየት አመጣህው ከማለት ውጭ የተለየ ምርመራ ሳይደረግበት ነው ዛሬ የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ የተፈታው። የእምዬ ምኒልክ ምስል ያለበት ቲሸርት መልበስም ሆነ ማሰራጨት ወንጀል ባለመሆኑ ለመክሰስ አልቻሉም ብሏል። አካሄዱን አሳዛኝና አሳፋሪ መሆኑን የገለፀው ሄኖክ አክሊሉ የኢትዮጵያ ባለውለታ የሆኑት የራስ መኮንን ሀውልት በፈረሰባት የሀረር ከተማ የመንግስት አካሄድ ገና ከጅምሩ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሷል፤ በሚመለከተው አካል አስቸኳይ እርምት እንዲሰጥበትም ጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply