በሀሰተኛ የክፍያ ሰነድ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ዝውውር ወንጀል ተጠርጥረው ለእስር የተዳረጉት ቀሲስ በላይ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ

መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው የ7 ቀን ጊዜ ውስጥ የምስክሮችን ቃል መቀበሉን፣ በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ኤሌክትሮኒክስ ምርመራ እንዲደረግ ለሚመለከተው ተቋም መጠየቁን፣ የቴክኒክ ምርመራ እንዲሰጠው በደብዳቤ መጠየቁን አስታውቋል።

በተጨማሪም በቀሲስ በላይ ሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ብርበራ ማድረጉንና በብርበራ የተገኘ የጦር መሳሪያ ህጋዊነት የማረጋገጥ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል፤ ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጾ መርማሪ ፖሊስ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

ቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ ሌሎቹም ተጠርጣሪዎች በ6 ጠበቆች ተወክለው ችሎት የቀረቡ ሲሆን ደንበኞቻቸውን ተጨማሪ በእስር ለማቆየት የሚያስችል አይደለም በማለት ተከራክረዋል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የ8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።

ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply