በሀዋሳና ሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ልጆችን በነጻ ለማስተማር ቃል ገቡ።በሀዋሳና ሻሸመኔ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች እንዳላቸው የቅርንጫ…

በሀዋሳና ሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ልጆችን በነጻ ለማስተማር ቃል ገቡ።

በሀዋሳና ሻሸመኔ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች እንዳላቸው የቅርንጫፍ ብዛት ተማሪዎችን ተቀብለው እንደሚያስተምሩ ነው ትምህርት ቤቶቹ ለኢትዮ ኤፍ ኤም የተናገሩት።

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት ምክንያት የመቃጠል አደጋ የደረሰበት ሻሸመኔ የሚገኘው ሉሲ ትምህርት ቤት ባለቤት አቶ ዮሀንስ ወልዴ ባሉን አምስት የማስተማሪያ ቅርንጫፎች አንድ አንድ ተማሪ እንቀበላለን ብለዋል።

ልናስተምር ቃል የገባነው ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም ከደረሰብን ኪሳራ አንጻር ነገሮች ሲስተካከሉልን ሌሎች ተማሪዎችን እንጨምራለን ብለውናል።

የትምህርት ቤቶቹ ዳይሬክተሮች ከዚህ ቀደም ቤተሰብ የሌላቸውንና ችግር ላይ የወደቁ ተማሪዎችን እናስተምራለን እንጂ እንዲህ ያለ መልካም ተግባር ላይ አልተሳተፍንም ለዛም ነው ጥያቄውን በቶሎ የተቀበልነው ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ልጆችን ተቀብለው በነጻ ለማስተማር ቃል የገቡት ቢኤንቢ፣ ሉሲ፣ ዩኒየን ማውንት፣ ኦሊቭና ኤስ ኦኤስ ትምህርት ቤቶች ናቸው።

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply