በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ የሆነው የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው

በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ የሆነው የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ የሆነው የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው።
ፋብሪካውን የሚያስገነባው አማ ቢዝነስ ግሩፕ ሲሆን ÷ ለሚያስገነባው ኘሮጀክት የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል።
በዚህ ወቅት የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሀገራችን ኢኮኖሚ ፓሊሲ የግል ባለሀብቶችን የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸው በክልሉ ማልማት ለሚፈልጉ ሌሎች ባለሀብቶች ሁሉ ምቹ ሁኔታ መኖሩን በመግለጽ ጥሪ አቅርበዋል።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር አቶ መላኩ አለበል እንደሀገር ለዘይት ምርት በየወሩ 48 ሚሊየን ብር እንደሚወጣ ገልጸዋል።
የሀገራችን የዘይት ፋብሪካዎች 12 በመቶ ብቻ የሚሸፍኑ መሆኑን የተናገሩት አቶ መላኩ ኘሮጀክቱ እንደ ሀገር የዘርፉን ችግር የሚቀርፍ መሆኑን አስረድተዋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ረዳት ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በበኩላቸው÷ እንደነዚህ አይነት ኘሮጀክቶች ስራ አጥነትን ከመቀነስ አንጻር የጎላ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው የከተማዋንም ተመራጭነት እንደሚያሰፉ ተናግረዋል።
ከተሞችን ለሰው ልጆች ምቹ ለማድረግ አስተዳደሩ ጠንክሮ እየሰራም ነው ብለዋል ምክትል ከንቲባው።
የድርጅቱ ባለባት አቶ አንድነት ጌታቸው እንደ ሀገር በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ወደ ኢንቨስትመንት መግባታቸውን ገልፀው የዚህ ኘሮጀክት ግንባታ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር እንደሚፈጅ ተናግረዋል።
ድርጅቱ በፍጥነት እንደሚጠናቀቅ እና ለ2 ሺህ44 ሰዎች ቋሚና ጊዛዊ የስራ እድል እንደሚፈጠርም መናገራቸውን ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ የሆነው የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

Leave a Reply