በሀዲያ ዞን ኮሌራ መከሰቱ ተሰምቷል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን የኮሌራ በሽታ መከሰቱን ሰምተናል።

በዞኑ በሚገኘው የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ታካሚዎች መኖራቸውንም ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሆስፒታሉ ሰራተኛ ነግረውናል።

ከዚህ በፊት ወደ ሆስፒታሉ የመጡ #2 ሰዎች ናሙናቸው ተወስዶ በተሰራ ምርመራ በሽታው እንዳለባቸው መረጋገጡን እና አሁን ላይ #5 ታካሚዎች በሆስፒታሉ መኖራቸውንም አንስተዋል።

ታካሚዎቹ ከአንድ አከባቢ የመጡ ናቸው ያሉን ባለሙያው በአከባቢው የውሃ ዕጥረት መኖሩ ለህመሙ መነሻ ምክንያት ሆኗል ብለውናል።

በሆስፒታሉ ድንኳኖችን በመትከል ለማከም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ያነሱት ባለሙያው ፤ ከኩፍኝ ወረርሽኙ ያላገገመው ሆስፒታል አሁንም በስራ መጨናነቁንም ነው የገለፁት።

በዞኑ ከዚህ ቀደም ብሎ የኩፍኝ ወረርሽኝ ተከስቶ የሰዎችን ህይወት መንጠቁ የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ ግን በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን አንስተውልናል።

የዞኑ የጤና ቢሮ ሃላፊዎች ከዚህ በፊት ኩፍኙን #ለመደበቅ እንደሞከሩት ኮሌራውንም ለመሸሸግ እየሞከሩ ነው ያሉት ባለሙያው ፤ ናሙና ተወስዶ ውጤት ከመጣ በኋላ መደረግ ያለበት የህክምና አገልግሎቱን ማፋጠን ነበር ብለዋል።

ይሁን እንጂ እስከ አሁን ምንም የተደረገ ድጋፍም ሆነ ሌላ እንቅስቃሴ የለም ያሉ ሲሆን፤ ለሰራተኛውም ደሞዝም ሆነ ምንም ዓይነት ክፍያ እንዳልተከፈለው አንስተዋል።

የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች ወረርሺኞች ሲከሰቱ የሚከፈል የትርፍ ሰዐት ክፍያን ጨምሮ ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ያሰሙትን ቅሬታ ባሳለፍነው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል።

በእስከዳር ግርማ

የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply