በሀገረ ማሪያም ኮረማሽ አካባቢ የሚገኘዉ የአጼ ሚኒሊክ የጦር ካምፕ የዉሀ እና የመብራት አገልግሎት ተደራሽ ባለመሆኑ በሚፈለገዉ ልክ ቱሪስቶችን ለማስጎብኘት እንዳልተቻለ ተገለጸ፡፡

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ማሪያም ወረዳ ኮረማሽ አካባቢ የሚገኘዉ የአጼ ሚኒሊክ የጦር ካምፕ ከአድዋ ድል በኃላ የተሰፈረበት ቦታ እንደሆነ የሀገረ ማሪያም ከሰም ወረዳ የቅርስ ጥበቃ እና ቱሪዝም ልማት ሃላፊ አቶ ደስታ ታደሰ ግልጸዋል፡፡

ኮረማሽ ተብሎ የሚጠራዉ ይህ አካባቢ የአጼ ሚኒሊክ የጦር ካምፕ የቱሪስት መስህብ ለማድረግ በሚደረገዉ ጥረት በስፋራዉ የመብራት እና የዉሀ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት ለቱርስት መስህብ ለማድረግ መቸገራቸዉንም አቶ ደስታ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡በጦር ካምፑ ያሉ ቤቶችም ከዚህ ቀድም 14 የነበሩ ቢሆንም በጊዜ ሂደት ጥገና ባለመደረጉ ሰባቱ መፍረሱንም ገልጸዋል፡፡

ቀን 08/06/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply