በሀገሪቱ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተገለጸ፡፡በሀገራችን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/kzVZjFw9RZh0bBt2a6Oknjep11ogUtNnhsYcEwo86vVFKgGU4Vm0WaprC94XMXxUZcUtQShsvWVwKWWq5NY8vuMlP7-lQPo32f5U_LewdbaS9WLXS8S0Y9CiqnKHfZKGB1TmDmf7LhG6eyGQ-We2DeNZqKcU_vJ691LCYcQkDQdL17Z1obHqUgK-0CtJ2Xy3CvT_0M65TdDcrrHVIZz2RwuMiL-ZYQ_9j3B06VlPuhUeU24FnzFaZUT5xsF3AroBmu57ZLaA7_hLhw3iA93JMJrpe_sXNnUuOrwqmYrAQD35IfFAEhPEyvjUzhG3bMvKtWauxjLvyBOzL4_0nBctdw.jpg

በሀገሪቱ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተገለጸ፡፡

በሀገራችን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ ለጣቢያችን ገልፀዋል።

ዋናው ምክንያት ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ስርዓት እንደሆነ የጠቆሙት ዶክተር አየለ በተለይ በምግብ ውስጥ ጨው ማብዛት፣ በቂ አካላዊ እንቅስቃሴ ያለማድረግ፣ ስጋን ጨምሮ የእንስሳት ውጤቶችን አብዝቶ መመገብ፣ ስኳር የበዛበት ጣፋጭ ምግቦች ማዘውተር፣ አልኮልና ትንቧሆ በዋናነት አጋላጭ መንስኤዎች ናቸው ብለዋል።

የበሽታዎችን መስፋፋት በህክምና መቀነስ እንደማይቻል አመልክተው፤ በዋናነት 50 በመቶ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻለው አጋላጭ መንስኤዎች በማተኮር መስራት ሲቻል መሆኑን አስረድተዋል።

ለዚህም በቂ አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግና የአመጋገብ ስርዓት ከማሻሻል ባሻገር ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት ማበጀት ወሳኝ መሆኑን ተናግሯል

ዶክተር አየለ እንደሃገር በሺታ የመከላከልና ጠና ማበልጸግን ትኩረት ተደርጎ በተወሰነ መልኩ ደግሞ የፈዉስ ህክምና ለመስጠት ባለፉት ጊዜያት እየሰራን ነበረ ብለዋል፡፡

ከፍተኛ የመዳኒትንና የህክምና መስጫ መሳሪያዎችን ለማስገባት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረትና የሰለጠነ የሰው ሃይል ከገጠሙን ችግሮች መካከል ናቸው ብለዋል።

በልዑል ወልዴ

የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply