በሀገራችን ለዜጎች መፈናቀልና ላለው ሁኔታ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት  ኃላፊነት መውሰድ አለበት ሲሉ ታማኝ በየነ ተናገሩ (አሻራ ጥር፡-14/05/13/ዓ.ም ባህር ዳር በሀገራችን ላለው ሁ…

በሀገራችን ለዜጎች መፈናቀልና ላለው ሁኔታ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ኃላፊነት መውሰድ አለበት ሲሉ ታማኝ በየነ ተናገሩ (አሻራ ጥር፡-14/05/13/ዓ.ም ባህር ዳር በሀገራችን ላለው ሁ…

በሀገራችን ለዜጎች መፈናቀልና ላለው ሁኔታ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ኃላፊነት መውሰድ አለበት ሲሉ ታማኝ በየነ ተናገሩ (አሻራ ጥር፡-14/05/13/ዓ.ም ባህር ዳር በሀገራችን ላለው ሁኔታ በስልጣን ላይ ያለው መንግስትና እያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት መውሰድ አለበት ያለው ታማኝ በየነ ሰው በማንነቱና በእምነቱ የሚገደልበት ሁኔታ ያሳቅቃል፡፡ መንግስት ይህንን ለማስቀረት ብዙ ሥራ መሠራት አለበትም ብሏል ፡፡ በኢንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ላይ የተገኘው አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አርቲስት ታማኝ በየነ የኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት የሁሉንም ድርሻ ይጠየቃል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ምንም የማያውቁ ንጹሀና በገዛ መሬታቸው ላይ መጤ ተብለው ሲገደሉ ሲሳደዱ፣ መስማትና ማየት እጅጉን ከባድ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ አፈር ጭረው አድረው ኢትዮጵያን እዚህ ያደረሱ፣ መከራን የተቀበሉ፣ ለዘመናት ከሰለጠነ ኃይል ጋር ሁሉ ተዋግተው ሀገር እንደ ሀገር ያስረከቡን አያት ቅድመ አያቶቻችን፣ በአንድነት ተቻችለው ኖረው በኛ ዘመን መደማመጥና መቻቻል ለምን አቃተን? ብለን መጠየቅ አለብንም ሲሉም አክለዋል፡፡ አያይዘውም ሀገር እንደሀገር እንድትቀጥል ያደረገውን ህዝብ መግፋትና ማሳደድ ዋጋ እንደሚያስከፍልም አመላክተዋል፡፡ በጅምላ የሚነዳ በጋራ የሚያስብ፣ የተማረ አይደለም ያሉት ታማኝ በየነ በሀገራችን ውስጥ ያለው ከፍተኛ አደጋ የተፈጠረው በጅምላ በሚያስቡ አካላት እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ማንነት ማንም በጉልበት ሊነጥቁ የሚያስቡ አካላት፣ የተሳሳተ መንገድ እየተከተሉ መሆኑን አመላክተው ማንነታችን ከእኛው ጋር አብሮ የሚኖር እንጅ ማንም እንደፈለገ ሊያደርገው የሚችል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ የዜጎች ሞትና መጎዳት እያንዳንዳችንን ሊያመን ይገባልም ያሉት ታማኝ በየነ ያለምንም ጥፋታቸው የሚራቡና ሜዳ ላይ የወደቁ ዜጎችን ማሰብ መቻል ሰብአዊነት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የተማሩ ወጣቶች ሀገራችንን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው ገልጸው መንግሥት ሕዝብ የሚፈልገውን ማድረግ እንደሚገባውም ተናግሯል፡፡ ሕዝብ ካመጸ ከፍተኛ ችግር ሊፈጠር ስለሚችል ይህ ከመምጣቱ በፊት መንግስት ሕዝብ የሚፈልገውን ማድረግ እንዳለበት አመላክተዋል፡፡ በመጨረሻም የተጎዱ ዜጎችን ለመደገፍ ምን ማድረግ አለብን በሚለው ጉዳይ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር እንደተወያዩም ተናግሯል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply