በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያ አካባቢዎች በተለይ ደግሞ በመተከል በወለጋና በጉራ ፈርዳ በአማራው ላይ የሚደርሰውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያወግዝ ታላቅ_የተቋውሞ_ሰልፍ  በዩናይትድ ኪንግደም…

በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያ አካባቢዎች በተለይ ደግሞ በመተከል በወለጋና በጉራ ፈርዳ በአማራው ላይ የሚደርሰውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያወግዝ ታላቅ_የተቋውሞ_ሰልፍ በዩናይትድ ኪንግደም…

በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያ አካባቢዎች በተለይ ደግሞ በመተከል በወለጋና በጉራ ፈርዳ በአማራው ላይ የሚደርሰውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያወግዝ ታላቅ_የተቋውሞ_ሰልፍ በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ተጠራ አሻራ ሚዲያ 2/08/13/ዓ.ም ባህር ዳር ሰሞኑን በተለያ የሀገራችን ክፍሎችና በተለያዩ የዓለም ሀገራት በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እንዲቆም ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ አሁንም በመተከልና በወለጋ ንጹሀን አማራዎች በዘር በሀይማኖታቸው ተለይተው አሰቃቂ ግድያ እና ከፍተኛ እንግልት እየተፈጸመባቸው ስለሚገኝ መንግስትም በንጹሀን አማራዎች ላይ የሚደርሰውን ግፍና በደል በችልተኝነት እየተመለከተው ስለሆነ ይህንን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፎች ቀጥለው ይገኛሉ፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ በአማራ ብሄር ላይ እየተፈፀመ ያለውን በመንግስት ሙሉ ድጋፍ የሚታገዘው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ዘመቻን በማውገዝ ለወገናችን ድምፅ እንሁን በማለት በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ሰልፍ ተጠርቷል፡፡ የሰልፉ ዋና አላማ መንግስታዊ መዋቅር ባለው ኦነግ ሸኔና በጉምዝ ልዩ ሀይል እንዲሁም በአንዳንድ የኦሮሞ ብልጽግና አመራሮች ትዕዛዝ ሰጭነት አማካኝነት በአማራ ላይ የሚደርሰውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚቃወም እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሰልፉ ላይም በአማራ ላይ የሚደረገው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቁም የሚሉ መፈክሮች እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ STOP! AMHARA GENOCIDE IN ETHIOPIA A CALL FOR PROTEST AGAINST THE ETHIOPIAN GOVERNMENT ETHINC CLEANSING OF AMHARA IN ETHIOPIA PLACE: 10 DOWNING STREET, WESTMINSTER, LONDON, SW1A 2AB DATE: TUESDAY 13 April 2021 TIME: 13:00pm – 18:00pm 13 April 2021, ከቀኑ 13፡00 ሰዓት – 18፡00 Contact: 07949532646 / 07957311117 / 07984109189

Source: Link to the Post

Leave a Reply