በሀገራችን የሚደረጉ ውሳኔዎችን ኦህዴድ/ሙሉ በሙሉ ባይደመድምም ብአዴንንና ሌሎች ድርጅቶችንም ያገለለ የተናጠል ስምምነት እንደሚያደርግ ተገለጸ፡     አሻራ ሚዲያ ጥር፡-14/…

በሀገራችን የሚደረጉ ውሳኔዎችን ኦህዴድ/ሙሉ በሙሉ ባይደመድምም ብአዴንንና ሌሎች ድርጅቶችንም ያገለለ የተናጠል ስምምነት እንደሚያደርግ ተገለጸ፡ አሻራ ሚዲያ ጥር፡-14/…

በሀገራችን የሚደረጉ ውሳኔዎችን ኦህዴድ/ሙሉ በሙሉ ባይደመድምም ብአዴንንና ሌሎች ድርጅቶችንም ያገለለ የተናጠል ስምምነት እንደሚያደርግ ተገለጸ፡ አሻራ ሚዲያ ጥር፡-14/05/13/ዓ.ም ባህር ዳር ስልጣን አጋሩኝ ለማለት የሚፈራዉ ብአዴን የአማራን ወጣት ካስፈጀ ብኋላ የኦህዴድ ሀይል በኢትዮጵያ ላይ ሙሉ ለሙሉ ያነግሰዋል:: አማራም መታረዱን መሳደዱን: በ አረመኔዎቹ ኦህዴድ አንዴ በማጅራት አንዴ በአንገቱ መታረዱን ይቀጥላል:: ኦህዴዳዉያን አማራን አርደዉ አይተዉትም:: ደሙን እጃቸዉን ይታጠቡበታል ለጣኦት ይሰዉታል ይለናል ሸንቁጥ አየለ:: ስልጣን አጋሩኝ ለማለት የሚፈራዉ ብአዴን ፋኖ ወያኔን አባሮ ስልጣን እጁ ላይ ቢያስገባለት ስልጣኑን ሁሉ ወስዶ ኦህዴዳዉያን አስረከበ:: ቀደም ሲል ወደ የገዱ ቲም አሜሪካ በሄደ ሰዓት በዉጭ በሚኖሩ ጉጉ አማራዎች ገዱን ስልጣን ከኦህዴድጋር ትጋራላችሁ? የሚል ጥያቄ ተነስቶላቸው ነበር፡፡ በዚህን ስዓት አቶ ገዱእኛ ስልጣኑ አያሳስበንም::ስልጣን አንፈልግም ብለው መመለሳቸውን ምንጫችን ያወሳል፡፡ ብአዴን ፋኖ ላይ ከኦህዴድ: እንዲሁም ከብርሃኑ ነጋ ኢዜማ ጋር ሆኖ ፕሮፖጋናዳ ከፈተ:: ፋኖ የሚባል አያስፈልግም:: የታጠቀ አያስፈልግም:: ፋኖ አክራሪ ነዉ:: መጥፋት አለበት የሚል ፕሮፖጋንዳ በደንብ ተጧጧፈ::እንዳሉትም ፋኖን ማሰር:በጅምላ መግደል:ማሳደድ: መወንጀል እና ማሸማቀቅ እንደያዙ ምንጫችን ይናገራል:: አሁንም ከዚህ ዉጊያ ብኋላ የሚሆነዉ እየሆነ ያለውንም ሸንቁጥ እንደሚከተለው አስቀምጧል ፡፡ 1.ብአዴን ስልጣን አጋሩኝ ብሎ የኦህዴድ ጌቶቹን አይጠይቅም::ቢጠይቅም ስልጣን አያቀምሱትም ይለናል: : እንዲሁም ስልጣን አጋሩን የሚል የብአዴን ባለስልጣን ከተገኘ እንደ አሳምነዉ ኦህዴዳዉያን የሆነ ሰበብ ፈጥረዉ ይገሉታል ወይም እርስ በርስ ተገዳደሉ ብለዉ እራሳቸዉ ያጠፏቸዋል ሲልም ከትቦታል:: ይሄም የሚሆነዉ ብአዴን ውስጥ ያሉ ሰዎች የአማራ ህዝብ ሞት የማያሳስባቸዉ ኢትዮጵያን ለመምራት ወኔ ቢስ ስለሆኑ እና የሚራወጡትም ለጊዜአዊ ሆዳቸዉ ስለሆነ ተማምነዉ የሚሰሩት ሚስጢር ስለሌለ ነዉ እንደሆነም ያስቀምጣል፡፡ 2. ብዙ ግዜ እንደምናየው ይላል ጽሀፊው የክልሉን አብዛኛዉን ወጣት እና ፋኖን ጦርነት ይማግዱታል:: የቦንብ ማምከኛም ያደርጉታል ብሏል:: 3.በተቃራኒው ደግሞ ኦህዴድ የራሱን ወታደር ማሰልጠኑን አጠናክሮ ይቀጥላል:: ከሚያሰለጥነዉ ወታደርም አንድ አስረኛዉ እንኳን ወደ ጦርነቱ ግንባር አይገባም:: 4.ከጦርነቱ ብኋላ የኦህዴድ እብሪት ይበልጥ አብጦ እና ፈርጥሞ ይገኛል:: የሽመልስ አብዲሳንም አማራን ፈጽሞ የማጥፋት እቅድ በስፋት ተግባራዊ እየሆነ እንደሚገኝ አመላክተዋል:: 5.ሰላም እንዲሰፍን ሀገር እንደሀገር እንድትቀጥል ዜጎች በነጻነት ሀሳባቸውን እንዲያራምዱ ትልቅ ሚና የተጫወቱ ተቃዋሚዎችም ጥያቋ መጠዬቅ ሲጀምሩ ተሰብስበዉ ልክ እንደ ሰላማዊዉ ታጋይ እስክንድር ነጋ ወደ እስር ቤት ይጣላሉ:: 6.በሀገራችን በሚደረጉ ውሳኔዎችን ኦህዴድ ሙሉ በሙሉ በበላይነት ባይደመድምም ብአዴንና ሌሎችንም ያገለለ የተናጠል ስምምነት እንደሚያደርግ ሸንቁጥ አየለ ገልጸዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ መፍትሄው ብአዴን እራሱን በፍጥነት ከኦህዴድ ማላቀቅ እንዳለበት ጽሀፊው ያስቀምጣል:: የራሱን ሰራዊት እራሱ ማደራጀት እንዳለበትም ያመላክታል፡፡ ከኦህዴድ እዝ ስር በፍጹም አለመግባት:: መዋጋት ካለበትም በራሱ ቀመር እና በራሱ ስትራቴጂ ብቻ መዋጋት አለበት ሲልም ያስቀምጣል :: ብአዴን እራሱን ከኦህዴን ከለየና የራሱን ሰራዊት ማደራጀት : መምራት: ማሰልጠን እና ማዋጋት ከቻለ በአስተማማኝነት ከጦርነቱ ብኋላ የአማራ ህዝብን ህይወት የሚታደግ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን አንድነት በርግጠኝነት የሚያስጠብቅ ሀይል ሆኖ ይወጣል ሲል ሸንቁጥ አየለ አስቀምጧል::

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

 1. Mamo

  This is an insightful article by Shenqut Ayele. ADPs it is a recommendable article that you should take it seriously. Wake up from your deep sleep. Look around cautiously what is happening around you, assess the political realities of past , present so that you be able to more or less accurately predict the future politics of this country. Have the courage to challenge the shrewd odps that are misleading you under the guise of ” a united ” Ethiopia but the reality is the other way round. Do this as soon as possible, not tomorrow, the time is today.

Leave a Reply