በሀገራችን 106 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች የኤች አይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ መኖሩን አያቁም ተባለ፡፡

በሀገራችን ከ6 መቶ 10ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች የኤች አይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ አንድ መቶ 6 ሺህ የሚሆኑት ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ መኖሩን እንኳ እንደማያውቁ የጤና ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል፡፡

የኤች አይቪ ቫይረስ ስርጭት ዛሬም ቢሆን በማህበረሰቡ ላይ የኢኮኖሚ፣ የጤና እና ማህበራዊ ችግሮችን እያስከተለ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

በሀገራችን የኤች አይቪ የስርጭት መጠን 0.91 በመቶ ሲሆን 610 ሺህ 350 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን በበሽታው እንደ አዲስ የሚያዙም ከ8 ሺህ 200 በላይ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

የስርጭቱ ምጣኔው ከክልል ክልል የሚለያይ ሲሆን፤ ከፍተኛው ጋምቤላ 3.69 በመቶ ፣ በአዲስ አበባ 3.47 በመቶ እንዲሁም ዝቅተኛው ሶማሌ 0.18 በመቶ መሆኑ ተመላከቷል፡፡

በክልልም ያለው ምጣኔ ከቦታ ቦታ እንዲሁም በማህበረሰብ ክፍሎችም እንደሚለያይ የተጠቆመ ሲሆን፤ በበሽታው ከሚያዙ ሰዎች ከ11 ሺህ300 በላይ የሚጠጉ ሰዎች እንደሚሞቱ ተገላክቷል፡፡

በሀገራችን በ2030 የኤች አይቪ ስርጭት የማህበረሰብ ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ለማድረስ የተለያዩ ስራዎች እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡
ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን አድሎ እና መገለል ለማስቀረት የማህበረሰቡ ተሳፎ ከፍተኛ ሚና እዳለው በማመን የማህበረሰቡት ተሳትፎ ለማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሚገኝም ኢት ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው
ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply