በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሂደት ላይ የሙስሊሞች ውክልና አነስተኛ ነው ሲል የኢትዮጵያ እስልማና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅሬታውን አሰማ፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከኢትዮጵያ…

በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሂደት ላይ የሙስሊሞች ውክልና አነስተኛ ነው ሲል የኢትዮጵያ እስልማና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅሬታውን አሰማ፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ቀጥሎ አጀንዳ ያስገባ ተቋም መሆኑንም ጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ከጣብያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው የምክር ቤቱ የሙስሊሞች ምክክር ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ሀጂ ኑረዲን ጀማል አጀንዳውን ለኮሚሽኑ ስናስገባ ኮሚሽኑ በደስታ እንደተቀበላቸውና ጥሩ ግንኙነት እንዳላቸው ተናግዋል፡፡

ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ህዝበ ሙስሊም ቁጥር ያማከለ ውክልና በኮሚሽኑ ውስጥ አለመኖሩ ቅሬታ እንደተሰማቸው ለጣብያችን ገልፀዋል፡፡

“ከመጀመሪያውም ቅሬታችን ማህበረሰብ ነው የተደራጀው የሚል ሀሳብ ኮሚሽኑ ቢኖረውም በተወከሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ ሀይማኖትን አላማከለም” የሚለው ቅሬታ እንደተሰማው የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አንስቷል፡፡

“በሀገሪቱ ውስጥ በአሁን ሰዓት ካሉት ማህበራት ሁሉ ቀድሞ ሀይማኖት ነበር ይህንን ስራ ቀድሞ ከወረዳ ጀምሮ ሳይወክል በክልል ደረጃ መደረጉ ትክክል አይደልም” ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

“ሙስሊሞች ካልተሳተፉ የሙስሊሙን ጥያቄ ማን ሊያነሳው ይችላል?” የሚሉት ሀጂ ኑረዲን ከኮሚሽኑ ጋር ጥሩ ግንኙነት ቢኖራቸውም የተሳትፎው ጉዳይ እንዲፈታ እንደሚፈልጉ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከሀገራዊ ምክከር ኮሚሽኑ ጋር በዚህ ዙሪያ ምክክር ያደረገ ቢሆንም መፍትሄ አለመኑሩን ለማወቅ ችለናል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለ 9 አጅንዳ 47 ጥያቄዎች ማስገባቱ የተገለፀ ሲሆን፣
ከአጀንዳዎቹ መካከልም በሀገሪቱ ለረጅም ግዜ የቆየው የገዢ እና ተገዢ ትርክት መቆም አለበት ኢትዮጵያን የገነቧት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው ስለዚህ የሁሉ ተሳትፎ ጎልቶ ይቅረብ፣ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ መሆኑ በግልፅ ምክክሩ ሊፈታው የሚገባ ነው የሚልም ተካቶበታል፡፡

ሌላው የሀገር ጀግኖች ላይ እና በትምህርት መማሪያዎች ላይ ያለው የሙስሊሙ ሚና መካተት አለበት የሚልና በተለይም ከህዝብ ቆጠራ ጋር ተያይዞ ሙስሊሙ ሁል ግዜ 33 በመቶ ብቻ ነው የሚለው በትክክል ተቆጥሮ ትክክለኛ ቁጥሩ ሊቀመጥ ይገባል የሚሉ አጀንዳዎች እንደተካከቱበት ጣብያችን ሰምቷል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply