በሀገር ቤት ትግል ላይ የዲያስፖራ አስተዋጽኦና ተጽዕኖዉ ======= ሸንቁጥ አየለ ======== በሀገር ቤት የትግል ሂደት ላይ የዲያስፖራ አስተዋጽኦና ተጽዕኖን አንዳንድ ሰዎች የሚገመግሙት…

በሀገር ቤት ትግል ላይ የዲያስፖራ አስተዋጽኦና ተጽዕኖዉ ======= ሸንቁጥ አየለ ======== በሀገር ቤት የትግል ሂደት ላይ የዲያስፖራ አስተዋጽኦና ተጽዕኖን አንዳንድ ሰዎች የሚገመግሙት በአዎንታዊ ገጽታዉ ብቻ ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ደግሞ በአሉታዊ ጎኑ ብቻ ይገመግሙታል። ሆኖም ግምገማዉ በሁለቱም ጠርዥ በስፋት ሊታይ ይገባዋል። አዎንታዊ ገጽታዉ === ኢትዮጵያ እንደሃገር እንዳትቆም ካደረጋት አንዱ እዉነታ በስፋት የተማረዉ የሰዉ ሀይሏ ወደ ዉጭ መኮብለሉ ነዉ።በሌላ አባባል ዲያስፖራዉ በርካታ የ አእምሮ ጉልበት ያለዉ ሃይል አለዉ ማለት ብቻ ሳይሆን በዉጭ ሀገርም ጉልበት ያለዉ ኢኮኖሚ እጁ ዉስጥ አለ ማለት ነዉ።ሁለትም ያልተማራዉ ዲያስፖራም እንኳን ቢሆን በተሻለ አቅም ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል። በተለይም ዲያስፖራዉ ከገንዘብና እዉቀት በተጨማሪም የሚዲያና መረጃ ጉልበት አለዉ ቢባል ማጋነን አይሆንም።ከዚሁም ጋር ተያይዞ በርካታ የመሰባሰቢያ ማህበራትን ለመመስረት ያለዉ ነጻነት እና ምቹ ሁኔታ ሌላዉ የዲያስፖራዉን ጉልበት ወሳኝ ቦታ እንዲኖረዉ የሚያደርግ እዉነታ ነዉ። ስለሆነም በሀገር ቤት በሚደረገዉ የፖለቲካ ሂደት ዉስጥ የዲያስፖራዉ ሚና ቁልፍ ነዉ። አሉታዊ ገጽታዉ ======= የዲያስፖራዉ ተጽእኖ በዋናነት የሚመነጨዉ ዲያስፖራዉ ራሱ ለመተዋወቅ አለመቻሉ ላይ ነዉ።ዲያስፖራ እርስ በርሱ ለመተዋወቅ ፈተና የሚሆንበት እንደ ግለሰብ/እንደ ቡድን/አለመተዋወቁ ብቻ አይደለም።የእዉቀት አለመሳለጥ፡ የራ እይ መጣረስ፡ የስሜት አለመዋዋጥ እና በመሃል የሚራወጠዉ አንዱ ስለሌላዉ የሚያወራዉ የስማ በለዉ ወሬ ነዉ። የዲያስፖራ ነጽሮተ አለም ወጥ በሆነ ማህበረሰባዊ የጋራ እሴት ያልታሸ፡ በተገመደ የጋራ ራዕይ ያልተሳሰረ እና በጋራ ስሜት ታሽቶ ያልተዋዋጠ ነዉ። ይሄም የሚያስከትለዉ ብዙ መዘዝ አለ።ከሁሉም የከፋዉ ግን ለመለያዬት የፈጠነ እና እኔ አዉቃለሁ ባይ የበዛበት ሁኔታን መፍጠሩ ነዉ።በዚህም የተነሳ በርካታ አካሂያድ፡በርካታ ስብስብ ይፈጠራል።ለአንድ አላማ እንታገላለን የሚሉም በትንሽ ነገር ተጣልተዉ ሁሉ በሃገር ቤት የራሱን ቡድን በማጀገን እና የርሱ ያልሆኑትን በማጥላላት ላይ የማተኮር ዝንባሌ የሀገር ቤቱን ትግል ፈተና ዉስጥ ይከተዋል። የሀገር ቤት ታጋዮች ከዲያስፖራዉ ጋር በምን መልክ ቢሰሩ ዉጤታማ ይሆናሉ? ============= የሀገር ቤት ታጋዮች የመጀመሪያ ስራ ተቋማዊ ስርአት ማበጀት መሆን አለበት።የዉጭ ግንኙነቱንም በስርኣት እና በተመደበዉ ተወካይ በኩል ማድረግ አለባቸዉ።ከሁሉም በላይ የዉጭ ግንኙነት ዘርፉ የድርጅቱን ዉስጠ ሚስጢር ጠልቆ እንዳያዉቅና በዲያስፖራ በኩል የሚመጡ የደህንነት ስጋቶችን መቋቋም እንዲችል መሰልጠን አለበት።የድርጅቱ ዋና አመራሮች እና የድርጅቱን ሚስጢር የሚያዉቁ ሰዎች በሙሉ ከዲያስፖራ የድጋፍ ሀይል ጋር እንዳይገናኙ ተደርገዉ ስርአት ሊበጅላቸዉ ይገባል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply