በሀገር አቀፍ ደረጃ ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን የመመርመርና ህክምና የማስጀመር ንቅናቄ ይፋ ሆነ

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን የመመርመርና ህክምና የማስጀመር ንቅናቄ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን የመመርመርና ህክምና የማስጀመር ንቅናቄ ይፋ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የጤና ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ኮቪድ19 ወረርሽኝ በጣም ከጎዳቸው አገልግሎቶች መካከል አንዱ ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን የመመርመር ስራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በ2020 ለመድረስ ከታቀደው 90 በመቶ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎችን የመመርመር እቅድ 79 በመቶ ብቻ እንደተከናወነ ጠቅሰው በቀጣይ ስድስት ወራት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የፌዴራል ኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር ጄኔራል ዶክተር ፅጌረዳ ክፍሌ በበኩላቸው÷ በቀደሙት አመታት በተገኘው መልካም ውጤትና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የታየው መዘናጋት ችግሩን አባብሶት መቆጣጠር ወደማይቻልበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት በተለይ በምርመራና ልየታ ጠንካራ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ መግለፃቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ይፋ የተደረገው ሃገር አቀፍ ንቅናቄ ለስድስት ወራት እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በሀገር አቀፍ ደረጃ ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን የመመርመርና ህክምና የማስጀመር ንቅናቄ ይፋ ሆነ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply