በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሚዲያዎች አሁንም የአማራ እና የትግራይን ህዝብ የሚነጣጥል የውሸት ፕሮፓጋንዳ  እየተሰራጨ መሆኑ ተመላከተ፡፡  (አሻራ ጥር 14፣ 2013 ዓ.ም)  ህወኃት  የሰሜን…

በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሚዲያዎች አሁንም የአማራ እና የትግራይን ህዝብ የሚነጣጥል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየተሰራጨ መሆኑ ተመላከተ፡፡ (አሻራ ጥር 14፣ 2013 ዓ.ም) ህወኃት የሰሜን…

በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሚዲያዎች አሁንም የአማራ እና የትግራይን ህዝብ የሚነጣጥል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየተሰራጨ መሆኑ ተመላከተ፡፡ (አሻራ ጥር 14፣ 2013 ዓ.ም) ህወኃት የሰሜን እዝን ላይ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ማዕከላዊ መንግስቱ በህወኃት ላይ ማጥቃትን መሰረት ያደረገ ጦርነት አድርጎ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የህወኃት ሀይልን ደምሷል፡፡ ህወኃት ወደ አማራ ክልል በቀጥታ ጦርነት ከመክፈቱ በተጨማሪ ፣ 5 ሮኬቶችንም ወደ አማራ ክልል ወርውሮ የሰው ህይዎት እና ንብረት አውድሟል፡፡ 3 ሮኬቶችን ወደ ባህርዳር አከታትሎ ልኮ የባህርዳር በላይዘለቀ አየር ማረፊያን የመታ ሲሆን ፣ የሰው ህይዎትም እንዲያልፍ አድርጓል፡፡ ይሄን ተከትሎም የአማራ ልዮ ሀይል በወሰን አካባቢ ከመከላከያ ጋር ሆኖ ህግ አስከብሯል፡፡ ከዛ ውጭ ግን ወደ መቀሌ እና አዲግራት ሂዶ ንፁሃንን ቀርቶ ከህኃወት አመራሮች ጋር ጦርነት አልገጠመም የሚል ሀሳብ ከአማራ ክልል ሰላም እና ደህንነት መረጃ አግኝተናል፡፡ ነገር ግን መሰረቱን አውሮፓ ያደረገ የካቶሊክ ማዕከላዊ የዜና ወኪል ( catholic centeral news agency) አክሱም ፅዮን በአማራ ልዮ ሀይል ተመታች ሲል ፅፏል፡፡ በአክሱም ፅዮን ሲሳለሙ የነበሩ 750 አካባቢ ንፁሃንንም በመከላከያ እና በአማራ ልዮ ሀይል ተገደሉ ሲል የሰባዊ መብት ተከራካሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡ በዚህ ጉዳይ አስተያይታቸውን የሰጡን አንድ ከፍተኛ የፀጥታ አመራር “እንኳን አክሱም ፅዮን እና ንፁሃንን የአማራ ሊጎዳ ቀርቶ፣ የአማራ ልዮ ሀይል አክሱም አልገባም” ብለዋል፡፡ የአማራ ህዝብ እና የትግራይ ህዝብን በክርስትናው ከሚያስተሳስሩ ጉዳዮች አክሱም ፅዮን አንዷ ናት፡፡ ሁለቱ ህዝቦች አይነጣጠሌነታቸው የሚታየውም በእምነት ተቋሞቻቸው እና በባህላቸው ነው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ደግሞ አልነጃሽን የጋራ መንፈሳዊ ሀብት አድርጎ የአብሮነቱ መሰረት አድርጎታል፡፡ ይህ ሆኖ እያለ ህዝብን ከህዝብ ለመነጠል ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ የሚቃቅር መረጃ እየተለቀቀ መሆኑ አስተዛዛቢ ነው ሲሉ የፀጥታ ሀይሉ ለአሻራ ገልፀዋል ፡፡ በሌላ በኩል የአማራ ብልፅግና አመራር እና በዙሪያው ያለው ሀይል ሀሳብ አልባ እና ቅርብ አዳሪ ስለሆነ እንጂ የትግራይን እና የአማራን ህዝብ ዕርስ በዕርስ ማገናኛው ጊዜ አሁን ነበር ሲሉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ሀሳባቸውን ለአሻራ ገልፀዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተጣሉ ቁጥር ህዝብ መቃቃር የለበትም፡፡ ህዝብ ለህዝብ ወንድም እንጂ ጠላት አይደለም ያሉት እነዚህ ተንታኝ፣ የሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት በህወኃት የጥላቻ ፖለቲካ ምክንያት የጠየመ እንዳይሆን አሁንም መነጋገር አስፈላጊ ነው፡፡ የሰሜን ፖለቲካ እንዲደክም እና ሁለቱ ህዝቦችን እስከ መጨረሻው በመነጣጠል ሲሰጋጉ እንዲኖሩ ለማድረግ የሀገር ውስጥ የሴራ ፖለቲከኞች እየሰሩበት እንደሆነም አሻራ ሰምቷል፡፡ በአማራ ላይ የተዘራው የጥላቻ ፖለቲካ የሚራገፈው የአማራ ፖለቲካ ሲያሸንፍ ነው የሚሉት እኒህ ተንታኝ፣ የአማራ ፖለቲካ እንዲያሸንፍ ደግሞ የታቀደ እና የተብራራ ትንታኔ፣ መተግበር የሚችል አስፈፃሚ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ነገር ግን የአማራ ብልፅግና ለአሸነፈው ሁሉ ምቹ በመሆን፣ የአማራን ህዝብ ፍላጎት ማንፀባረቅ ሲሳነው ተስተውሏል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply