
ከተቀሰቀሰ ከአንድ ወር በላይ የሆነው የሱዳን ጦርነት እየተባባሰ እንደቀጠለ ነው። በሁለቱ ጄኔራሎች በሚመሩት ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት ከተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ቀናት አንስቶ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን እና የውጭ አገር ዜጎች ከአገሪቱ እየተሰደዱ ነው። ከእነዚህም መካከል በርካታ የውጭ አገር ዜጎች ወደ አገሮቻቸው ተመልሰዋል። በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኤርትራውያን ግን ወደ አገራቸውም ሆነ ወደ ሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ አልቻሉም።
Source: Link to the Post