በሁለት ወለጋ ዞኖች ውስጥ 195 ሺህ ሰው ተፈናቅሏል

ከምሥራቅ ወለጋና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ከ195 ሺህ በላይ ሰው ባለሥልጣናቱ “ሸኔ” በሚሏቸውና ራሳቸውን “የኦሮሞ ነፃነት ጦር” ብለው በሚጠሩ ታጣቂዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ኃላፊ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ከተፈናቃዮች መካከል አንዳንዶቹ “ያፈናቀሉን የመንግሥት ኃይሎች፣ ፋኖና የነፃነት ታጋዮች ነን የሚሉ ሸኔዎች ናቸው” ሲሉ ከስሰዋል።

የኦሮምያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ተጠይቀው “ባለፈው ጥቅምት አማርኛ ተናጋሪ ፅንፈኞች ሲቪሎችን ገድለዋል፤ ያሁን መፈናቀል ያስከተለውን ግድያ የፈፀሙት ግን የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” ብለዋል።

ታጣቂዎቹ ከዚህ ቀደም መንግሥት የሚያነሳባቸውን ወቀሳ አይቀበሉም።

በሌላ በኩል የኦሮምያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራራር ኮምሽን በምስራቅ ወለጋና ለሌሎችም ዞኖች ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮችን ለመመለስ እየሰራን ነው ብሏል።

በዚህ ዙሪያ ከሰላም ሚኒስቴር አመራሮች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply