በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲሰለጥኑ የነበሩ ምልምል ወታደሮች የምረቃ ስነስርዓት ተካሄደ

በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲሰለጥኑ የነበሩ ምልምል ወታደሮች የምረቃ ስነስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲሰለጥኑ የነበሩ ምልምል ወታደሮች የምረቃ ስነስርዓት ተካሄደ።
በዝግጅቱ ላይ የመከላከያ የሰላም ማስከበር ማዕከል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ተመራቂ ምልምል ወታደሮችም በክብር እንግዶቹ ፊት የተለያዩ ወታደራዊ ትዕይንቶች አቅርበዋል።
ሰልጣኞቹ በፍላጎታቸው ወደ መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀልና መስፈርቱን በሟሟላት በዛሬው ዕለት በየማሰልጠኛ ተቋሙ መመረቃቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል።
ተመራቂ ምልምል ወታደሮቹ የአካል ብቃት፣ የተኩስና የስልት ስልጠናዎችን በመውሰድ ከፍተኛ አቅም መገንባታቸውን በተግባር እንዳሳዩ መገለፁን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ተመራቂ ምልምል ወታደሮች ሁርሶ፣ ጦላይና ብርሸለቆ በሚገኙ የወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ናቸው።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲሰለጥኑ የነበሩ ምልምል ወታደሮች የምረቃ ስነስርዓት ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply