You are currently viewing በሂደቱ መስማማት አለመስማማት ሌላ ነገር ነው። ላመነበት ሀቅ በመታመን ግን እስክንድር ነጋን የመሰለ የነፃነት ታጋይ የለም። የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣  ለጥቅም  አያደገ…

በሂደቱ መስማማት አለመስማማት ሌላ ነገር ነው። ላመነበት ሀቅ በመታመን ግን እስክንድር ነጋን የመሰለ የነፃነት ታጋይ የለም። የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ለጥቅም አያደገ…

በሂደቱ መስማማት አለመስማማት ሌላ ነገር ነው። ላመነበት ሀቅ በመታመን ግን እስክንድር ነጋን የመሰለ የነፃነት ታጋይ የለም። የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ለጥቅም አያደገድግም፣ ከርስን አወፍሮ ህሌናን ማስራብ አይወድም። ለሚኖርበት እና ለሚያደርገው ተገቢ ምክንያት አለው። ካመነበት ምክንያት ዝንፍ አይልም። አዲስአበባ ተወልዶ ፣ አሜሪካ አድጎ በተሻለ አኗኗር ውስጥ ልጅነቱን ያጣጠመ ቢሆንም የእሱ ምቾት ለሌላው ካልደረሰ ተመቸኝ ብሎ አይተኛም። ከ1985ዓም እስካሁን ሁሌም በትግል፣ ሁሌም በመታሰር እንዳለ አለ። እስሩም ቀጥሏል፣ እስክንድርም በራሱ እውነት ቁሟል። ያው የኛ ኑሮም በእንቧለሌ እንቅስቃሴ ውስጥ ሆኖ፣ ታሰረ ተፈታ፣ ተፈናቀለ ተመለሰ፣ ተጣሉ ታረቁ፣ መግለጫ ተሰጠ _የመግለጫው ቃል ታጣፈ፣ እከሌ እንዲህ ነው እከሌ እንዲያ ነው፣ በአንዱ መከፋት ሌላው እየሳቀ፣ የአንዱ ስደት ሌላው መኖሪያው ሆኖ ህይዎት በተቃርኖ ቀጥሏል። ከፍ ያለ የማህበረ ፖለቲካ መበሳበስ እና ምስቅልቅሎሽ ውስጥ ገብተናል። ከዚህ አዘቅት ለመውጣት ከጫጫታ እና ከደርሶ መልስ ስሜት የተላቀቀ ሁሉን የሚጠቅም መፍትሄ ያስፈልግ ነበር። © ጋዜጠኛ የሺሃሳብ አበራ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply