በሃራችን ከሚሰራጩ የስልክ ምርቶች መካከል ከ 50 በመቶ በላይ የሚሆኑት በኮንትሮባንድ የሚገቡ መሆናቸውን ሰምተናል

አገልግሎት ላይ ካሉ የስልክ ምርቶች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑ ወደ ሃገር የሚገቡት በህገ ወጥ መንገድ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት የኢኒስቲትዩት የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፌጤ በቀለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ እንዳሉት በስልክ መገጣጠም ስራ ላይ ተሰማርተው የሚሰሩ ወደ 30 የሚጠጉ ኩባንያዎች የነበሩ ቢሆንም፤በኮንትሮባንድ ንግድ ምክንያት ተዳክመው ሃያው ከስራ መውጣታቸውን ነግረውናል።

በአሁን ሰዓትም በዘርፉ ላይ የሚሰሩ 10 ኩባንያዎች ብቻ ናቸው ብለውናል፡፡

ከኮንትሮባንድ ንግድ በዘለለ፤ ከሃገር ውስጥ ግዢን መፈጸም አለመፈለግ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ኩባንያዎቹ ከስራ እንዲወጡ እና እንዲዳከሙ ምክንያቶች ስለመሆናቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ንግድ ሃገር ማግኘት ያለባትን ገቢ ጭምር እያሳጣት በመሆኑ፤ችግሩን ከወዲው ለመግታት ከጉሙሩክ ባለስልጣን ጋር በመቀራረብ እየሰራን ነው ብለዋል።

ማህበረሰቡ የሃገሩን ምርት መጠቀም እንዲችል የግንዛቤ ስራ በመስራት እና የምርት ጥራት ሂደቱን ለማሻሻል ተግባር ላይ ትኩረት አድርገው ከሚሰሩ የትምህርት ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢኒስቲትዩቱ በቅርቡ ስያሜውን “ ከብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩትነት” ወደ” ማንፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማእከል” በሚል እንደሚቀይር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፌጤ በቀለ፡፡

መሳይ ገብረ መድህን
መጋቢት 07 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply