በሃይማኖት ተቋማት እና በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚከፈቱ የስፖርት ውርርድ ቤቶች እየታሸጉ መሆኑ ተገለጸ ፡፡በሃይማኖት ተቋማት እና በትምህርት ቤቶች አከባቢ በ500 ራዲየስ ርቀት ዉስጥ የስ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/HCOL24Yw1PCAZ2j1XATGeis9JPBnqatLOIIQjqdUvR4KceLTjw6I3G0pn-vIBHjmkU9rJ_jxtIpk9Rrj-uhSj-SUL9JFf8SH632Kbz-suOYm-pth3v4rNntZTfxINS9tiyZN93jQnkZECOGcl8MIi62SrzHjvGtVE1zPqEaejv8Do9Tv3s4lIk6zx0UuTdUcdujzf8BbvtFYlNJsYBe90XcFrDyauHGZlYaWmKHfeTpfBU-6qpq1HUNvTwyZ5xWFQLyj5E9m_wTFFYoW8Lm5hpcrQJmtiH5xEhRQoeAcJ2Txgqckzjb8tLszQ0R8WlnMtkzfTD099zGOkJBykD5pEg.jpg

በሃይማኖት ተቋማት እና በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚከፈቱ የስፖርት ውርርድ ቤቶች እየታሸጉ መሆኑ ተገለጸ ፡፡

በሃይማኖት ተቋማት እና በትምህርት ቤቶች አከባቢ በ500 ራዲየስ ርቀት ዉስጥ የስፖርት ውርርድ የሚከፍቱ ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል።

በ500 ራዲየስ ርቀት ላይ የስፖርት ውርርድ ቤቶችን መክፈት የሚከለክል ህግ መኖሩን የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ነዋይ ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡

የተቀመጠዉን ህግ በመጣስ በሃይማኖት ተቋማት እና በትምህርት ቤቶች አከባቢ እንዲሁም በጫት ቤቶች እና በግሮሰሪ አቅራቢያ የሚከፈቱ የስፖርት ውርርድ ቤቶች መበራከታቸዉንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በመሆኑም ከመስፈርት ውጪ የስፖርት ውርርዶችን የሚያጫውቱ መኖራቸውን ተከትሎ ድርጊቱን በሚፈጽሙ ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

በእሌኒ ግዛቸው
ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply