በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሊባል የሚችል ከባድ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጓል፡፡የተሳካና ከባዱ ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገው ባልተለመደ መልኩ የሰውነት ክፍሉ ከመደበኛው በተቃራኒው ሆኖ…

በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሊባል የሚችል ከባድ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጓል፡፡

የተሳካና ከባዱ ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገው ባልተለመደ መልኩ የሰውነት ክፍሉ ከመደበኛው በተቃራኒው ሆኖ ለተወለደው የ 9 ዓመት ታዳጊ ነው፡፡

በኢትዮ ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል የህፃናት እና የአዋቂዎች የልብ ቀዶ ጥገና ሀኪም የሆኑት ዶክተር ሺቢቆም ታመነ፣ ለ9 ዓመት ታዳጊ ባልተለመደ መልኩ ልቡ በቀኝ በኩል ሆኖ ለተወለደው ታዳጊ በተሳካ ሁኔታ ቀዶ ጥገና መከናወኑን ተናግረዋል።

ለቀዶ ጥገና ህክምናው 5 መቶ ሺህ ብር መከፈሉ የተገለፀ ሲሆን፤ በውጭ ሀገር ቢሄድ ለቀዶ ለጥገናው ብቻ በትንሹ ከ 15 እስከ 20 ሺህ ዶላር እንደሚያስከፍል ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም ዜጎች ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ የሚያገኙትን የህክምና አገልግሎት ለማስቀረት ከ7 ዓመት በፊት ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን በሚል የልብ ቀዶ ጥገና በሀገር ውስጥ መሰጠት መጀመሩንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ዜጎች ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ለህክምና የሚያወጡትን ከፍተኛ ወጪ እና እንግልት ለማስቀረት ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የህክምና ባለሞያዎች፣ ወደ ውጭ ሀገር የሚያስኬዱ ህክምናዎችን በሀገር ውስጥ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡

ሆስፒታሉ በዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች በመታገዝ በአዋቂዎች እና በህፃናት የልብ ቀዶ ጥገና የሚሰጥ ሲሆን፤ በ8 ወራት ውስጥ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች ከፍተኛ የሆነ የቀዶ ጥገና አገልግሎት መሰጠቱ ተመላክቷል።

ማህበራዊ ኃላፊነት ከመወጣት አንፃርም 300 ለሚሆኑ ህፃናት የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና መስጠቱን በመግለጫው ላይ ተነስቷል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply