በሄይቲው የተሽካርካሪ ፍንዳታ የሞቱ ሰዎች ከ90 በላይ ሆኑ

ሂይቲ ውስጥ ባላፈው ሳምንት በአንድ የነዳጅ ተሽካርካሪ ቦቴ ላይ በደረሰ የፍንዳታ አደጋ ቆስለው የነበሩ በርካት ሰዎች በመሞታቸው በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ90 በላይ  መድረሱን የአገሪቱ ባለሥልጣንት ትንናት ሰኞ ባወጡት መግለጫ አስታውቁ፡፡

አደጋው የደረሰባት የካፕ ሄይቲ ከተማ ረዳት ከንቲባ አሁን ድረስ በአደጋው የሞቱትና ሊሞቱ የሚችሉትን ሰዎች ቁጥር አለመታወቁን ገልጸዋል፡፡ በርካታ ሰዎች ሆስፒታል እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ 

ቀደም ሲል በተሰጠው መግለጫ 75 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 47 የሚሆኑት ደግሞ ክፉኛ መቃጠላቸው ተነግሯል፡፡  አደጋው የደረሰው ታህሳስ 4 ቀን ሲሆን ነዳጅ የጫነው ተሽከርካሪ ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ፣ አንድ ታክሲ አድናለሁ በሚል የመገልበጥ አደጋ ስለደረበት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ በርካታዎቹ ሰዎች ላይ  የደረሰው የፍንዳታ አደጋ የተከሰተው ከቦቴው የፈሰሰውን ነዳጅ ለመቅዳት በሚሞክሩበት ሰዓት መሆኑም ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply