በህልውና ዘመቻው ተሳትፎ ላደረጉ የጤና ባለሙያዎችና በጎ ፈቃደኞች የደብረታቦር ጠቅላላ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እውቅና ሰጠ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ.ም…

በህልውና ዘመቻው ተሳትፎ ላደረጉ የጤና ባለሙያዎችና በጎ ፈቃደኞች የደብረታቦር ጠቅላላ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እውቅና ሰጠ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በህልውና ዘመቻው ለተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች እውቅና ለመስጠት ባለመው መድረክ ላይ በደቡብ ጎንደር ግንባር የልዩ ሃይልና የመከላከያ እንዲሁም ህዝባዊ ሰራዊቱን አቀናጅተው ሲመሩ የነበሩ ከፍተኛ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ስለመገኘታቸው ተነግሯል፡፡ አሸባሪው የትግራይ ቡድን በደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳንድ አካባቢዎች ሰርጎ በመግባት ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመቶች ማድረሱ ይታወሳል። ስለሆነም ይህ ወራሪ እና አሸባሪ ቡድን አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ከሰራዊቱ ጎን በመሆንና በመፋለም ረገድ ብዙ መስዋትነት የተከፈለ ሲሆን በዚህም የጤና ባለሙያዎች ትልቁን ድርሻ እንደሚወስዱ ተገልጧል። በመሆኑም የደብረታቦር ጠቅላላ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በህልውና ዘመቻው ላይ ተሳትፎ ያደረጉ የጤና ባለሙያዎችን፣የአንቡላንስ ሹፌሮችንና በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ በበጎ ፈቃድ ሲያገለግሉ የነበሩ ግለሰቦችን እውቅና ለመስጠት ለመስጠት ያለመ መድረክ ሆኖ መዘጋጀቱን ነው የደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን ዘገባ ያመለከተው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply