በህንድ የተመረዘ አልኮል የጠጡ 34 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

በደቡባዊ ህንድ በታሚል ናዱ ግዛት የሚገኙ 34 ሰዎች የተመረዘ አልኮል ከጠጡ በኋላ ህይወታቸዉ ማለፉ ተሰምቷል፡፡

ማክሰኞ ምሽት ላይ አልኮሉን የጠጡ ሰዎች መታመማቸዉን እና ህይወታቸዉ ማለፉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ወደ 80 ሰዎች በህክምና ተቋማት ዉስጥ እንክብካቤ እየተደረገላቸዉ ነዉ የተባለ ቢሆንም የአከባቢዉ ባለስልጣናት ግን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

ከሰዎቹ ሞት ጋር ተያይዞ 2 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ የተገለጸ ሲሆን፤ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ምርመራ እንደሚካሄድም ተነግሯል፡፡

የግዛቱ ባለስልጣናት በተጨማሪም አንድ ከፍተኛ የፖሊስ ባለስልጣን እና አስር የክልሉን ክልከላ ማስፈጸሚያ ክንፍ አባላትን በግዴለሽነታቸዉ ምክንያት በክልሉ ህገወጥ አልኮል እንዲዘዋወር ፈቅደዋል በማለት ከስራ አግደዋቸዋል፡፡

ነገር ግን የተቃዋሚ ፓርቲዎች መንግስት በግዛቱ ውስጥ ያለውን መርዛማ አልኮል መቆጣጠር አልቻለም ሲሉ ተችተዋል።

በህንድ ውስጥ በየዓመቱ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ከጎዳና ላይ በሚገዟቸዉ የአልኮል መጠጦች ምክንያት ህወታቸዉ ያልፋል፡፡

እስከዳር ግርማ

ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply